Monday, October 29, 2012


   ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን ?  ክፍል 6
    ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?
ከዚህ ቀደም ባቀረብናችው ጽሁፎች  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደ ማይመለከታት ቅዱሳን አባቶቻችን የተናገሩትን መመልከት ጀምረን ነበር በዚህ ጽሁፋችንም ቀጣዩን ክፍል እንመለከታለን  አምላካችን ልዑል እ ግዚአብሔር የእናቱን በረከት ረድኤት ያሳድርብን አሜን
  ቅዱስ  ኤራቅሊስ  በሃይማኖተ  አበው ምዕራፍ  48 ቁጥር 31  ስለ እመቤታችን ንጽህና ሲመሰክር እንዲህ ይላል 
     « ኢያእመረ እስመ ዘተፈጥረት እምነ ጽቡር ጽሩይ ትከውን  መቅደሶ ለእግዚአብሔር »ትርጉም « የእግዚአብሔር መቅደሱ ማደርያው ትሆነው ዘንድ ከንጹህ አፈር (ዘር)የተፈጠረች  መሆኗን አላወቀም  »