Saturday, August 11, 2012

መልክዐ ተክለሃማኖት

   ክፍል ሶስት  መልክዐ ተክለሃማኖት
፪    ሰላም ለዝክረ ስምከ በጥንተ ፊደሉ መስቀል  ስም ክቡር ወስም ልዑል። ተክለሃማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል ከመ እወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል። ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል። 
ትርጉም  << የስምሀ መነሻ ፊደል የመስቀል ምልክት ለሆነው እና ክቡር ገናና ለሆነው ስም አጠራርህ ሰላም እላለው ። የወንጌል ተቀዳሚ ስም ማቴዎስ የተባልክ ተክለሃይማኖት ሆይ እንደ ችሎታዬ አመሰግንህ ዘንድ አንደበቴ ትፈታልኝ ዘንድ ድንግል ማርያምን እማልዳለሁ።  >>