Friday, April 6, 2012

«ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም» ለምን ተባለ ?

           "ወአልብክሙ ተስፋ ድኂን ዘእንበለ መቃብሪሁ»                              «ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም»      ክፍል አንድ 
"ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር እንድወስድ እሺ ትለኝ ዘንድ እለምንሃለው     እግዚአብሔርም  ለኔ ለባሪህ በዚህ  ነገር ብቻ ይቅር ይለበለኝ" ፪ነገሥ፭፤፲፯

         ይህ ቃል  መኮንኑ ንዕማን ውደነብዩ ኤልሳዕ ሄዶ ታአምራት ከተደርገለትበኋላ ያቀረበው ጥያቄ ነበር። ነብዩ ኤልሣዕም ሃሳቡን ተቀብሎ በደኅና ሂድ ብሎ አስናብቶታል ። 
      ንዕማን በአገሩ እግዚአብሔር አይመለክም ስለዚህም ለአምልኮተ እግዚአብሔር ይረዳው ዘንድ የእግዚአብሔር ሰው ኤልሣዕ ካለበት ስፍራ አፈር ጭኖ ይዞ ሄደ በዚህም ይቅርታ ምህረት እንደሚያገኝ አመነይህ ማለት ዳነ ማለት አይደለምን? መዳን ማለት እኮ መደ አምልኮተ እግዚአብሔር መመለስ ለእግዚአብሔር እየተገዙ መኖር ማለት ነው ።

በሆሣዕና በዓል ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

      በሆሣዕና በዓል  ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው 
                                                                      
ሆሣዕናማለትምንማለትነው? 
መልስ ሆሣዕና ማለት መዳኃኒት ማለት ነው
 ፪ ጌታ በአህያ እና በውርንጫ በአንዴ እንዴት ሊቀመጥ ቻለ?  
መልስ     በሁለቱም በአንድ ጊዜ በታአምራት ተቀምጦባቸዋል ይህም ምሳሌ ነው አህያ የቤተ እስራኤል ውርንጫ የአህዛብ    ምሳሌ ሲሆኑ ጌታችን     በሁለቱም የሰው ዘር ሊያድር እንደመጣ ያስረዳል
፫  በሆሣዕና ለምን ዘንባባ ይደረጋል?
  መልስ   በወቅቱ ጌታ በአህያ እና በውርንጫ ተቀምጦ ወደኢየሩሳሌም ሲገባ ህጻን አዛውንቱ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው አመስግነውታል ያንን ለማስታወስ ሲሆን ምሳሌነቱም ዘንባባ ጫፉ እሾኻም ነው እሳት አይበላውም ጌታ ባህሪው የማይመርመር ኃያል መሆኑን ያስረዳናል
ጌታ አህያና ውርንጫይቱን ፈታችሁ አምጡልኝ ለምን አለ
  
መልስ    አህያይቱና ውርንጫዋ ተሰርቀው 
መታሰራቸውን የሚያውቅ ጌታ ፈታችሁ - አምጡልኝ አለ ማንም ቢጠይቃችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ አላቸው ይህም ምሳሌ ነው አህያ እና ውርንጫዋ የአዳምና የልጆቹ ምሳሌ ሲሆኑ መሰረቃቸው የሰው ሊጆች በኃጢአት ምክንያት ዲያቢሎስ ሰርቆአቸው ስለነበር ነው መፈታታቸው በጌታችን የሰው ልጆች ሁሉ ከበደል ከእዳ እስራት ነፃ መውጣታቸውን ያስረዳናል
   ተጨማሪ ከሆሣዕና ሊያስተውሏችው የሚገቡ ነጥቦች እነሆ 
በሆሣዕና ጡት የሚጠቡ ሕጻናት ምስጋናን አቅርበዋል ዛሬም ሕጻናት ከ፵እና ፹ ቀናቸው ጀምሮ የሆሣእናውን ጌታ እንዲያመሰግኑ ከማኅበረ ክርስትያኑ ጋር ይቀላ 
"ከሕጻናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ"መዝ፰፤፪-
በሆሣዕና ጌታ በተናቀች አህያ ተቀምጦ አክብሮአታል ዛሬም በትህትና በንስሃ ብንቀርብ ጌታ ያድርብናል ያከብረናል
  "ለጌታ ያስፈልጉታል" ማቴ፳፩፤፫    ነውና የተባለው ሁላችንም ለጌታ እናስፈልገዋለን የሁላችንንም መዳን ጌታ ይፈልጋል በሰው ዘንድ ታናናሽ የተባሉት ሳይቀሩ ለጌታ የማያስፈልግ የለም ስለዚህም ስለሁሉ እንጸልይ ሁሉ ተፈተው ወደ ጌታ እንዲመጡ የተቻለንን አስተዋጽዎ ማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችን ነው
            ከሆሣዕና በረከት ሁላችንንም ያሳትፈን
               የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን

Thursday, April 5, 2012

ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?

ካለፈው የቀጠለ 
          ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን? 
           ፪. የቅዱስ ገብርኤል ብስራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ (የዘር ኃጢአት ) እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ክፍለን ማየት እንችላለን
                " ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው
                   አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ"  ሉቃ ፩፣ ፳፰  
ግሩም ከሆነው የመልአኩ የምስጋና ቃል ውላዲተ አምላክ  ኃጢአት የሚባል ጨርሶ እንደማያውቃት ሶስት ጥልቅ የሆኑ መልእክቶችን እንመልከት
               ፪.፩" ጸጋ የሞላብሽ ሆይ" እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት እመቤታችን ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው
        "ሁሉ  የእግዚአብሔር ክብር (ጸጋ )ጎሎአቸዋል" ሮሜ፫፤፳፬ 
እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሰሩ አይደለም ነገርግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው 
   "ኃጢአት ባልሰሩት  ላይ እንኳን ሞት ነገሰ " ሮሜ፭፤፲፬ ተብሎ የተጻፈው ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ? ይህ በርግጥም እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊት ነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ ሳይሆንለት  ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው
                 ፪.፪ ከሴቶች መካከል 
ሁለተኛው ነጥብ ድንግል ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ ሌሎች የሰው ልጆች መጽሓፍ ቅዱስ ሲገልጽ 
         " ልዩነት የለም ሁሉ ከበደል በታች ናቸው" ሮሜ፫፤፳፪    ይላል
ስለእመቤታችን ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም ወላዲተ አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ።  እመቤታችን ከብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን? አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽህይት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ 
                   ፪.፫ የተባረክሽ ነሽ
በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ የሚለው ኃይለ ቃል ነው  በጣም የሚገርመው በዚሁ ተመሳሳይ ቃል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም በተመሳሳይ ስፍራ ምስጋና ቀርቦለታል
   "አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው"ሉቃ፩፤፵፪
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለንና እመቤታችንም ይተባረክሽ ነሽ ጌታም የተባረከ ነው የሚል ተምሳሳይ ምስጋና ቀርቦላቸውል ይህ ማለት ሁለቱንም  የጥንቱ መርገም እንደማይመለከታቸው ያመልክታል የበረከት ተቃራኒ መርገም ነው ስለዚህም የተባረክሽ ነሽ ማለት መርገም የሌለብሽ ነሽ ማለት ሲሆን ጌታ ደግሞ የተባረከ ነው ሲባል መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው። ልዩነቱን ልብ እንበል እምቤታችን የተባረክሽ ስትባል ከእናቷ ማህፀን ጀምሮ ልጇ ከምርገም ጠበቃት ማለት ሲሆን እርሱ ጊን የተባረከ ነው ሲባል ለባህሪው መርገም የማይስማማው ከሌሎች መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው።
     በአጠቃላይ ድንግል ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከስጋዋ ስጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለምሆን ያዘጋጃት በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ በምክንያትነት ወደፊት በቀጣዩ ክፍላችን የምንመለከተው ይሆናል 
                                                             ሰላመ እግዚአብሔር ኩሁላችን  ይሁን 
                                                                                     ይቆየን   

</a><ቀጣዩን በክፍል ሶስትንለማንበብ ይህንን ይጫኑ /a>

Wednesday, April 4, 2012

ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢያት ይመለከታታልን ?

ድንግል ማርያምን ጥንተ አብሶ [የዘር ኃጢአት]ይመለከታታል?
                                     ከእነምክንያቱ ብታብራሩልኝ
    ክፍል አንድ       

  ድንግል ማርያም የዘር ኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው የሚከተሉትን    ሶስት ነጥቦች እንመለከታለን     
                                     ፩.አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት [ጥንተ አብሶ ] እንደሌለባት አስረግጠው ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል                                     ፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ «እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ስዶም በሆንን እንደ ግሞራም በመሰልነ ነበር» ኢሳ፩፤፱ ዘር የተባለች ዓለም የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት ድንግል ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በእብራዊያን ክታቡ «የአብራሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም » እብ፩፤፲፮ በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳያስም እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት እመቤትችንን ነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ  ሔዋን ለይቶ በንጽሐ ስጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከስጋዋ ስጋ ከነፍስ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት             ፩.፪ ነብዩ ዳዊት « የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብይ ወገንሽን የአባትሽን በት እርሺ ንጉስ ውበትሽን ወዶአልና» መዝ፵፬፤፱-፲፩ ቼም ማንም ሊከራክር ቢወድ ከእመቤታችን በላይ ለሌላ ይህ ቃል ገላጭ በምንም መልኩ አያስከድም ይልቁንም በምስተዋል ላነበበው ድንግል ማርያምን የሚገልጽ ጥልቅ ትምህርት ማግኘት ይችላልወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ደርባ ደራርባ የተባለው ደግሞ ንጽሓ ስጋ ላይ ንጽሓ ነፍስ ንጽሃ ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ የዳዊት ሊጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ፩፤፩ ንጉስ የተባለ ልጇ እይሱስ ክርስቶስ ሲሆን ውበትትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው                   
 ፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን «ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም» መኃ፬፤፯ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹህ ነው ብሎ አመስግⶈታል ይቆየን              በክፍል ሁለት  ይቀጥላል 
<ቀጣዮን ለማንበብ ይህን ይጫኑ>