Thursday, April 5, 2012

ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?

ካለፈው የቀጠለ 
          ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን? 
           ፪. የቅዱስ ገብርኤል ብስራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ (የዘር ኃጢአት ) እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ክፍለን ማየት እንችላለን
                " ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው
                   አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ"  ሉቃ ፩፣ ፳፰  
ግሩም ከሆነው የመልአኩ የምስጋና ቃል ውላዲተ አምላክ  ኃጢአት የሚባል ጨርሶ እንደማያውቃት ሶስት ጥልቅ የሆኑ መልእክቶችን እንመልከት
               ፪.፩" ጸጋ የሞላብሽ ሆይ" እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት እመቤታችን ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው
        "ሁሉ  የእግዚአብሔር ክብር (ጸጋ )ጎሎአቸዋል" ሮሜ፫፤፳፬ 
እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሰሩ አይደለም ነገርግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው 
   "ኃጢአት ባልሰሩት  ላይ እንኳን ሞት ነገሰ " ሮሜ፭፤፲፬ ተብሎ የተጻፈው ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ? ይህ በርግጥም እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊት ነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ ሳይሆንለት  ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው
                 ፪.፪ ከሴቶች መካከል 
ሁለተኛው ነጥብ ድንግል ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ ሌሎች የሰው ልጆች መጽሓፍ ቅዱስ ሲገልጽ 
         " ልዩነት የለም ሁሉ ከበደል በታች ናቸው" ሮሜ፫፤፳፪    ይላል
ስለእመቤታችን ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም ወላዲተ አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ።  እመቤታችን ከብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን? አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽህይት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ 
                   ፪.፫ የተባረክሽ ነሽ
በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ የሚለው ኃይለ ቃል ነው  በጣም የሚገርመው በዚሁ ተመሳሳይ ቃል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም በተመሳሳይ ስፍራ ምስጋና ቀርቦለታል
   "አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው"ሉቃ፩፤፵፪
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለንና እመቤታችንም ይተባረክሽ ነሽ ጌታም የተባረከ ነው የሚል ተምሳሳይ ምስጋና ቀርቦላቸውል ይህ ማለት ሁለቱንም  የጥንቱ መርገም እንደማይመለከታቸው ያመልክታል የበረከት ተቃራኒ መርገም ነው ስለዚህም የተባረክሽ ነሽ ማለት መርገም የሌለብሽ ነሽ ማለት ሲሆን ጌታ ደግሞ የተባረከ ነው ሲባል መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው። ልዩነቱን ልብ እንበል እምቤታችን የተባረክሽ ስትባል ከእናቷ ማህፀን ጀምሮ ልጇ ከምርገም ጠበቃት ማለት ሲሆን እርሱ ጊን የተባረከ ነው ሲባል ለባህሪው መርገም የማይስማማው ከሌሎች መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው።
     በአጠቃላይ ድንግል ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከስጋዋ ስጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለምሆን ያዘጋጃት በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ በምክንያትነት ወደፊት በቀጣዩ ክፍላችን የምንመለከተው ይሆናል 
                                                             ሰላመ እግዚአብሔር ኩሁላችን  ይሁን 
                                                                                     ይቆየን   

</a><ቀጣዩን በክፍል ሶስትንለማንበብ ይህንን ይጫኑ /a>

2 comments:

  1. Tsegawun yabizalih; Emebrihan kefit tmirah kehuala tiketeli, Fitsamehin yasamire

    ReplyDelete
  2. Tsegawun yabizalih Emebrihan titebih kefit tmirah kehual tiketelih fitsamehin yamirew

    ReplyDelete