Thursday, April 19, 2012

ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?

ክፍል 3ካለፈው  የቀጠለ ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን? 
    ባለፈው የክፍል 1 እና ክፍል 2 ዝግጅታችን ማስነበባችን ይታወሳል በገባነው ቃል መሰረት ቀጣዩን ይዘን  ቀርበናል መልካም ንባብ      
3.እመቤታ ድንግል ማርያም የውርስ   ኃጢአት አለባት ማለት  የጌታችንን ንጹሐ  ባህሪውን መዳፈር ነው   
ጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ስጋና ነፍስን ከሰማይይዞ አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባህሪይ ተዋሕዶ ነውይህን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል"እንግዲህ ልጆቹ በስጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይስለጣንያለውንእንዲሽር-እንዲሁ ተካፈለ የአብርሃምን ዘር  ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም''ዕብ2፤14-15
   እንግዲህ ጌታ ሰው ሲሆን ስጋንም ነፍስንም ከድንግል ማርያም ከነሳእርሷ ደግሞ መርገም ነክቶአታል ከተባለ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታ  ኃጢአትያለበትን ስጋ ተዋሐደ ልንል ነውን?እንዲህማ ካልን ተረፈ አይሁድ ሆነናል ማለትነው ምክንያቱም ደፍረው  ጌታን ኃጢአት አለበት ያሉት አይሁድ ናቸውና 
 " ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛእናውቃለን" ዮሐ 924
         እኛስ ከእመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያላወቀውን ስጋ ደነሳ እንመሰክራለን እንደ እውነተኞቹ አባቶቻችን ጌታችን ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን እናምናለን እንመሰክራለን            " ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐተ ከመ አንስት እለ እምቅድሜኪ ወእምድሬኪ አላ በቅድስና በንጽሕና ስርጉት አንቲ "ርጉም"ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድመው ካንችም በኋላ እንደ ነበሩ ሴቶች አደፍ ጉድፍን የምታውቂ አይደለሽም  በቅድስና በንጽሕና ጸንተሽ ኖርሽ እንጂ"ቅዳሴ ማር542       
           መቼም አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የደረሱአቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት እጅግ ይከብዳል ፡፡ እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስትያን ስለነገረ ማርያም በጥንቃቄ የምታስተምረው ስለድንግል ማርያም የምናምነው ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከጌታችን ማንነት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው እግዚአብሔር ይግለጥልንና ጌታ ከእመቤታችን መርገም ያለበትን ስጋ ተዋሐደ ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ተቃርኖዎችን ያስነሳል።    ይቆየን
         ማሳሰቢያ
           ታድያ አንዳንዶች በቤተክርስትያኒቱ የሌለ አስተምህሮ በብሎጎቻቸው እና በመጻሕፍቶቻቸው የኦርቶዶክስ እያስመሰሉ አንዳንድ  ጥልቅ ግንዛቤ የሌላቸውን የዋሃን ክርስትያኖችን ለማሳሳት የሚያደርጉትን የስህተት ተልዕኮ አውቀን ልንጠነቀቅ እንደሚገባ ብሎጋችንን ለምትከታተሉ  ምዕመናን ሁሉ አበክረን እናሳስባለን         
ከዚህ በፊት ያለውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

No comments:

Post a Comment