ክፍል ሶስት መልክዐ ተክለሃማኖት
፪ ሰላም ለዝክረ ስምከ በጥንተ ፊደሉ መስቀል ስም ክቡር ወስም ልዑል። ተክለሃማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል ከመ እወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል። ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል።
ትርጉም << የስምሀ መነሻ ፊደል የመስቀል ምልክት ለሆነው እና ክቡር ገናና ለሆነው ስም አጠራርህ ሰላም እላለው ። የወንጌል ተቀዳሚ ስም ማቴዎስ የተባልክ ተክለሃይማኖት ሆይ እንደ ችሎታዬ አመሰግንህ ዘንድ አንደበቴ ትፈታልኝ ዘንድ ድንግል ማርያምን እማልዳለሁ። >>