Monday, June 25, 2012

ነገረ መላእክት ክፍል አንድ

 የተከበራችሁ አንባብያን ባለፈው ዝግጅችን ቅዱሳን ?ተፈጥሮአቸውን፤አማላጅነታቸውን፤ጸጋቸውን ፤ክብራቸውን ፤በአጠቃላይ በቅዱሳን  መላእከት ዙሪያ  ቅድሰት ቤተክርስቲያን ያላትን አስተምሮ እና

    መናፍቃን ስለቅዱሳን መላእክት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ለመዳሰስ  እንሞክራለን ብለን በገባነው ቃል መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ይዘን እንቀርባለን አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ያድለን  በስነፍጥረት  ትምህርት ከ22 ነገደ ፍጥረታት መካከል  አንዱ ነገድ  የመላእክት ነገድ ነው (1) 
እነዚህም በቅድሰትቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት መላእክት ቅዱሳን ይባላሉ ለመሆኑ ቅዱሳን መላእእክት ለምን ቅዱስ ተባሉ ? መላእክት ማለት ምንማለት ነው?ተፈጥሮአቸውን፤ አማላጅነታቸውን፤ ጸጋቸውን ፤ክብራቸውን ፤በአጠቃላይ በቅዱሳን  መላእከት ዙሪያ  ቅድሰት ቤተክርስቲያን ያላትን አስተምሮ እና መናፍቃን ስለቅዱሳን መላእክት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ለመዳሰስ  እንሞክራለን  አምላከ ቅዱሳን  ጸጋውን በረከቱን  ያድለን አሜን 
                                           1.     ለምን ቅዱስ ተባሉ                      
        ቅዱሳ መላእክት ለምን ቅዱስ ተባሉ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ቅዱስ የሚለውን ቃል አስቀድሞ መመለስ ግድ ይላል ቅዱስ የሚለው ቃል  ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ቅዱስ ፣ማለት ፣ክቡር ፤ምስጉን ፣ልዩ ፤ምርጥ፣ ንጹህ ፣ጽሩይ ማለት ሲሆን ቅዱሳን የሚለው ቃል ደግሞ ቅዱስ፡(ሳን፡ሳት፡ድስት)1 ለሚለው ቃል የብዙ ቁጥር መጠሪያ ሲሆን፤ቅዱሳት(2) ስንል ለስም ፤ለሀገር ማቴ4፥5፤ለመጻህፍት ሮሜ 1፥2፤ለሰዎችዳን7፥27፤ለመላእክት ዳን4፥9፤ለንዋየ ቅዱሳት ፤የሚቀጸል ሲሆን ለሁሉም እንደየአግባቡ ይተረጎማል ።ቅዱስ የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ወዳጆቹ አገልጋዮቹ ለእርሱ የተለዩ የተመረጡ የከበሩት በሙሉ ቅዱሳን ይባላሉ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ለርስቱ የተለዩ ለክብሩ የተመረጡት ግሩማን ንጹሐን ኃያላን ረቂቃን መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን ። ቅዱሳን መላእክትን ቅዱስ ስንል የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡራን መስጠታችን አይደለም።
             እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል ቅድስና የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ እርሱን እንደ አምላክነቱ እንደጌተነቱ ለእርሱ የሚገባውን ክብር እናቀርባለን ኢሳ 57፥15 ።በዚህ መሰረት እግዚአብሔር በባህሪው ንጹሕ ስለሆነ ንጹሐ ባህሪ ይባላል ፤ክቡር ስለሆነ የክብር አምላክ ይባላል፤ምስጉን ስለሆነ የምስጋና ጌታ ይባላል፤ጽሩይ ስለሆነ ጹሩየ ባሕሪ ይባላል ።ስለዚህ የቅድስና መሰረት በባህሪው ቅዱስ የሆነው አምላካችን በቅድስናው የጸና በመሆኑ ወዶና ፈቅዶ የቅድስናን ጸጋ ለፍጡራን እንዲደርሳቸው  አድርጓል ይህም ይታወቅ ዘንድ እኔ ቅዱስ ነኝ እና ቅዱሳን ሁኑ ዘሌ19፥2 .1ጴጥ1፥17 ሲል ማዘዙ በጸጋ (በስጦታ)ቅዱሳን እንዲባሉ ወስኗል ።ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲእህ ሲል መስክሯል ዳሩ ግን፦እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቹ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም በኑሮአቹሁ ሁሉ ቅዱሳን  ሁኑበማለት ለፍጥረታት የተሰጠውን የጸጋ ቅድስና በምግባር በሃይማኖት እንዲጠብቁት አባታዊ ምክሩን አስተላልፎአል።
                ቅዱሳን መላእክት ስንል የተቀደሱ ፥ የተመሰገኑ፥  የተመረጡ፥ ንጹሓን፥ የከበሩ መልክተኞች ፥አገልጋዮች ማለታችን ነው።ስለምን  ይህ ክብር ተሰጣቸው ብንል በሃይማኖታቸው፥ በተፈጥሮአቸው  ምክንያት ነው፤የቅዱሳን ክብር እግዚአብሔር አክብሮአቸዋል ።በአንጸሩም በጥርጥር ምክንያት ከክብራቸው የተዋረዱ ፥ጸጋቸውን የተገፈፉ በሥራቸው ውዱቃን የሆኑ ሰራዊተ አጋንንት ደግሞ እርኩሳን መላእክት ይባላሉ። 2ጴጥ 2፥4እግዚአብሔር ኃጥያትን ለአደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጣሉ አሳልፎ ሰጣቸው
                                         2.    የመላእክት  ተፈጥሮ
                   መላእክት በቀዳማይ ዕለት ከተፈጠሩት 8 ፍጥረታት መካካል አንዱ  በመሆናቸው ተፈጥሮአቸው እምኅበ አልቦ አካላዊ ብርሃን ፈጥሮአቸዋል ስለዚህ መንፈሳውያን ረቂቃን በመናቸው ስጋና አጥንት የላቸውም በመጽሐፍመላእክቱን መንፈስ የሚያደርግዕብ 1፩፥፮፲፬ ።ቅዱሳን መላእክት ስለተልዕኮአቸውና አግልገሎታቸው ከእሳት እና ከንፋስ ተፈጥረዋል የሚሉ ሊቃውንት አሉ ዕብ 1፥14 እና መዝ103፥4መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አግልጋዮቹን የእሳት ነበልባል ይህም ነፋስ ፈጣን ነው መላእክትም ፈጣኖች ናቸው ።እሳት ብሩህ ነው መላእክትም ብሩሃነ አእምሮ ናቸው ።እሳትእና ነፋስ ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው መላእክትም ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው ።ቅዱሳን መላእክት ሲፈጠሩ በነገድ መቶ በከተማ አሰር ሆነው ለባውያን ፤ነባቢያን ፤ህያዋን ሆነው ተፈጥረዋል ።(3)
   3.    ቅዱሳን መላእክት መቼ ተፈጠሩ ?
          ቅዱሳን መላእከት በቀዳማይ ዕለት እሑድ ለይኩን ብርሃን ባለ ጊዜ ስጋ የሌላቸው ረቂቃን ሆነው ተፈጥረዋል ።ክቡር ዳዊትም መላእክት ሁሉ አመስግኑት ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ብርሃን ሁሉ አመስግኑት እርሱ ብሎአልእና ሁሉም እርሱም አዝዞአልእና ተፈጠሩም መዝ148፥2-5 ሲቀሌምንጦስምበመጀመሪያው ቀን እሑድ ሰማይን እና መላእክትን  ሁሉ ፈጠርኵዋቸው ይህንንም ለሙሴ  አልነገርኩም ይላል ስለዚህ ለምስጋና እና ለቅዳሴ የተፈጠሩት መላእክት በመጀመሪያው ቀን ሲል በፍጥረት የመጀመሪያ ዕለት በዕለተ እሑድ መፈጠራቸውን ልናስተውል ይገባል።(4
4.    የቅዱሳን መላእክት ባህርይ     
       የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካካል አንዱ ስለትንሳኤ ሙታን ያስተማረው ትምህርት አንዱ ነው።ሰዱቃውያንም ስለትንሳኤ ከጠየቁት ጥያቄ አንዲቱ ሴትሰባት ባሎች ነበሯት ከእነሱ በመንግስተ ሰማያት ለማን ሚስት ትሆናለች ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸው መልስ እንዲህ የሚልነበርበትንሣኤስ እንደሰማይ መላእክትበሰማይአያገቡም አይጋቡምም በማለት መመለሱ የቅዱሳን መላእክት  ተፈጥሮአቸው ሕያዋን፥ ለባውያን፥ ሰማያውያን፥ መንፈሳውያን ፥ብርሃናውያን መሆናቸውን ያሳያል ።ሉቃ24፥39         ይቆየን 

       አስረጅ  ፥ 1.  አባ ጎርጎርዮስ የቤክ ታሪክ
                 2.   አለቃኪ ዳነወልድ ክፍሌ ስዋሰወ ግእዝ መዝገበ ቃላት
                 3.     በኅሩይ  ኤርአሚያስ መዝገበ ታሪክ አንደኛ መጽሐፍ  
                 4.  መጽሐፈ ቀለሚንጦስ
        የቅዱሳን መላእክት ተራዳሂነት እና አማላጅነት አይለየን።
               

2 comments:

  1. Kale Hiwot yasemalin! Betam konjo tsehuf new ketenanesh yefidel gedfetoch besteker. Yehe degmo kes eyale yemitarem new. Yalehin gize atabeh yehin yemesasele tsehuf eyasnebebken bemehonu ejig betam litemesegen yegebal. Ye Egziabher amlak fikir ena bereket ye Emebetachin ye Kidist Dengil Maryam amalajinet yekidusan Melaëkit tselotna bereketachew endihum fetan teradaënetachew ye Tsadkan Semaëtat redëtna bereketachew yedresih agelgelotihin yebark.

    ReplyDelete