Thursday, September 10, 2015

ዜና ህይወቱ ለድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ


                   የቤተክርስቲያን የቀን መቁጠሪያን ያዘጋጀ  ድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ  ነው!ድሜጥሮስ ማለት መስተዋት ማለት ነው፡፡ ሀገሩ እስክንድርያ ነው፡፡ አባት እናቱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋጎች ነበሩ፡፡ ላባቱ ወንድም ሴት ልጅ ነበረችው ሲሞት ልጄን ከልጅህ አትለይብኝ ብሎት አብሮ አሳድጓቸዋል፡፡አካለ መጠን ሲያደርሱ ዘመኑ አረማውያን የበዙበት አማንያን ያነሱበት ነበርና ከሌላ ብናጋባቸው ከሃይማኖት ከገቢረ ሠናይ ይርቃሉ፤ ሕገ ነፍስ ከሚፈርስ ሕገ ሥጋ ይፍረስ ብለው አጋቧቸው፡፡ በልተው ከጠገቡ ጠጥተው ከረኩ በኋላ ሥርዓተ መርዓዊ ወመርዓት ያድርሱ ብለው መጋረጃ ጣሉባቸው፡፡ እሷ አስቀድማ ድሜጥሮስ ያንተ ወንድምነት ለኔ የእኔ እኅትነት ላንተ አልበቃ ብሎ የባዕድ ሥራ እንሥራ አለችው፡፡ እኔስ የአባት የእናቴን ፈቃድ ልፈጽም ብዬ እንጂ ፈቃዴ አይደለም፤ በዚያውስ ላይ አንቺ ከፈቀድሽ ብንተወው እንችል የለምን? አላት እንተወው አለችው፡፡ እንኪያስ አንቺንም ለሌላ እኔንም ለሌላ እንዳያጋቡን መስለን እንኑር አላት፡፡ በዚህ ተስማምተው አንድ ምንጣፍ እያነጠፉ አንድ ዐጽፍ እየተገናጸፉ 48 ዘመን ኖሩ ፡፡ ምነውመኑ ይክል ሐቁረ. እሳት በሕጽኑ ይል የለምን እንደምን ይቻላል? ቢሉ ሕሩይ ለንጽሕና ነውና አንድም እሳቱን እንዲታፈኑ ማድረግ ለጌታ ይሳነዋልን? መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቀኝ ክንፉን ለርሱ ግራ ክንፉን ለርሷ አልብሶ አድሮ ሲነጋ በአምሳለ ርግብ በመስኮት ወጥቶ ሲሄድ ያዩት ነበር፡፡

Saturday, January 17, 2015

ጥምቀተ ክርስቶስ

            ተ ስ           
                            እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን
በኢትዮዽያ  አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርዓት  መሰረት በየዓመቱ ጥር 11  ቀን በታላቅ ድምቀት የጥምቀት በዓል ይከበራል ለመሆኑ ጥምቀት ምን ማለት ነውእና በሌሎች በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን                                                                            
 ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መላ ሰውነትን በተቀደሰ ውኃ መነከር ወይም መዘፈቅ ውሰጥ ገብቶ መውጣት መነከር መውጣት መቀበር ማለት ነው አንድ ሰው በመጠመቁ ክርስቶስን በሞቱ ይመስለዋል ይኸውም ተጠማቂው ከቅዱሱ ውኃ ሲነከር በክርስቶስ ሞቶ ሲመስለው ከውኃ ሲወጣ ደግሞ ክርስቶስን በትንሣኤው ይመስለዋል፤ በዚህም ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናል፡

Tuesday, January 6, 2015

ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ

                                        ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ   
 ንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ
ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዓቢየ ወለአለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ

           በድንቁርናና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ፍጹም እውቀት ተሰጣቸው፤ ሞት ባመጣው ምስል ሞትን በመምሰል ለነበሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍስ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው፤ በኃጢአት ለነበሩ ስርየት፤ በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተሰጣቸው ኢሳ. 92እግዚአብሔር የሁላችን አባት አዳምን በአርአያውና በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ባረከው ሁሉንም እንዲገዛ እንዲነዳ ሥልጣን ሰጠው፤ በረከቱን፣ ሥልጣኑንና ሲሳዩን ከሰጠው በኋላ ፈጣሪውን የሚያስታውስበት ትዕዛዝ አዘዘው፡፡ ትዕዛዙም የፈጣሪና የፍጡር መለያ፣ የአዛዥና የታዛዥ ገደብ፣ ሰው ለሕግ መገዛት እንደሚገባው ለማስረዳት የተደረገ እንጂ የስስት ወይም የንፍገት አልነበረም፡፡




ይህንን ደግሞ አዳምም ሆነ ሔዋን ያውቁታል፤ በምግብ እጦት እንዳይቸገሩ ግን በገነት ያሉትን አትክልት እንዲበሉ ከውኃውም እንዲጠጡ ፈቅዶላቸዋል፡፡ሰው ግን ከፍጥረት አክብሮ አልቆ ያነገሠውን እግዚአብሔርን አስቀይሞ በተሳሳተ ምክር ተመርቶ አትብላ የተባለውን ዕፀበለስን ስለበላ ከፈጣሪውም ትዕዛዝ ስለወጣ በዚህ ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡