ድንግል ማርያምን ጥንተ አብሶ [የዘር ኃጢአት]ይመለከታታል?
ከእነምክንያቱ ብታብራሩልኝ
ክፍል አንድ
ድንግል ማርያም የዘር ኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች እንመለከታለን
፩.አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት [ጥንተ አብሶ ] እንደሌለባት አስረግጠው ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል ፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ «እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ስዶም በሆንን እንደ ግሞራም በመሰልነ ነበር» ኢሳ፩፤፱ ዘር የተባለች ዓለም የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት ድንግል ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በእብራዊያን ክታቡ «የአብራሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም » እብ፩፤፲፮ በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳያስም እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት እመቤትችንን ነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ለይቶ በንጽሐ ስጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከስጋዋ ስጋ ከነፍስ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት ፩.፪ ነብዩ ዳዊት « የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብይ ወገንሽን የአባትሽን በት እርሺ ንጉስ ውበትሽን ወዶአልና» መዝ፵፬፤፱-፲፩ መቼም ማንም ሊከራክር ቢወድ ከእመቤታችን በላይ ለሌላ ይህ ቃል ገላጭ በምንም መልኩ አያስከድም ይልቁንም በምስተዋል ላነበበው ድንግል ማርያምን የሚገልጽ ጥልቅ ትምህርት ማግኘት ይችላልወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ደርባ ደራርባ የተባለው ደግሞ ንጽሓ ስጋ ላይ ንጽሓ ነፍስ ንጽሃ ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ የዳዊት ሊጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ፩፤፩ ንጉስ የተባለ ልጇ እይሱስ ክርስቶስ ሲሆን ውበትትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው
፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን «ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም» መኃ፬፤፯ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹህ ነው ብሎ አመስግⶈታል ይቆየን በክፍል ሁለት ይቀጥላል
<ቀጣዮን ለማንበብ ይህን ይጫኑ>
No comments:
Post a Comment