Thursday, December 27, 2012

                               ን ኮ 

                       በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
                  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታህሣሥ 19 ከከበሩት መላእክት አንዱ የሆነው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክበረ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት በመዝሙር በጸሎት በምስጋና በቅዳሴ በዝክር ይከበራል ይታሰባል። የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለሥቱ ደቁቅን ከዕቶነ እሳት(ከነደደ እሳት) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
          ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል ሉቃ 1፥20 
ታላቁ ነብይ ሄኖክ ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መሰክሯል << በባቦች ላይ በገነትም በጸድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው ፡፡>> ሄኖክ 6-7<< በሦስተኛውም  በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ  ቅዱስ  ገብርኤል ነው >>1014 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል
        ገብርኤል የሚለው ቃል የሁለት ቃለትውህድ ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ትርጉምም የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን መላእክትን ”ንቁም በበእላዌነ እስከ ንረክቦ ላምላክነ  አምላካችንን ፈጣሪያችንን እስከምናውቅ ድረስ ባለንበት በተረዳንበት ነገር ጸንትን እንቁም በማለት ያጽናና ያረጋጋበተወዳጁመልአክበቅዱስ ሚካኤል መሪነትየሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል  አድርጓል (አክሲማሮስ ገጽ.35) ራእ12፥7 ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ  አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ፡ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ”(ኢሳ.1416)በማለት ገለጠልን፡፡ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ነበሩ፡፡

               ቅዱስ ገብርኤል በብሉይ ኪዳን በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው(ዳን.5፡11)ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ መልአክ ነበር፡፡ ለዚህ ነቢይ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡(ዳን.9፡21-22) አሁንም ነቢዩ ዳዊት “አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብሰውብፁዕነው፡፡በልቅሶሸለቆ በወሰንኸቸውስፍራየሕግመምህርበረከትንይሰጣልና፡፡”(መዝ.83፡5-6)እንዳለውናቸው፡፡ 

       ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ  አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም  የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም አወስዳቸዋለሁ፤ከእኔም የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡”(ኢሳ.10፡13-14) ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤ “የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል” ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡
       በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤ ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን  “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን አንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡ የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረግ ልብሳቸው ከእቶን እሳት ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ፡፡ ትእዛዙ አስቸኳይ ነበርና እነርሱን ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት አመሰገኑት፡፡
 ንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር የሰው መልክ ያለው ነገር ግን አምላክን የሚመስል መልአክ ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን”(ዮሐ.11፡49) ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው ያለው በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ እርሱ ስለመሆኑ ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡

                    ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም  ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የአገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ፡፡(ዳን.3 በሙሉ)  ሊቀ ነቢያት ሙሴ<< እኝን እንዲረዱን እንዲጠብቁን እንዲያጽናኑን እና እንዲያማልዱን መላእክቱን በፊታችን ይልካል።በመላአክ ፊት ተጠንቀቁ ስሜ ከእነርሱ ስም ጋርአለ >> እና ብሎ የሰራዊት ጌታ ቅዱሳን መአእክትን እንዳከበራቸው አስተምሮናል
          ቅዱስ  ገብርኤል በአማላጅነቱ በጸሎቱ ለታመኑበት ፈጥኖ የሚደርስ በብለይ እና በሐዲስ ኪዳን በልዪልዩ ተልኮዎቹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጸና ሰለሆነ ጥበብ በመግለጽ በማጽናት በማብሰር ከመከራ በማዳን ከእሳት ወላፈን በመታደግ ከአንበሳ መንጋጋ በማትረፍ እና ትዕቢተኞችን በመቅጣት በመገሰጽ እውነተኛ ታዳጊ መልአክ መሆኑን አስመስክሯል ።ሰለስቱ ደቂቅን በሚያሰደንቀው ትንብልናው እንደታደጋቸው እንደተራዳቸው ዛሬም በጸሎቱ ለሚታመኑ ዝክሩን ለሚያደርጉ ድረሳኑን የሚደግሙትን በጸሎት በመዝሙር በቅዳሴ በልዮ ልዮ መንፈሳዊ ክብ በዓሉን ብናናክበር አማላጅነቱን የጸጠውን ጸጋ ብንመሰክር በበደላችን ምክንያት ከተግባረ ጽድቅ ለተሰደድን ስደተኞች ከባሕረ እሳት ለሰጠምን ኃጥያተኞች የምናመልከው ያባቶቻችን አምላክ ለመልአኩን ልኮ የእሳቱን ባሕር እንዲያሻግረን የሊቀ መላእክትየቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱ የሰለሰቱ ደቂቅ በረከታቸው  ይደርብ  
                                  ምንጭ   ደርሳነ  ገብርኤል 
                                              ሐመር  መጽሔት
                                                 ስምዓጽድቅ
                                                 ነገረ መላእክት ትምህርት

1 comment:

  1. kale hiwot yasemalin yelike-melak kidus gebrial rediet yasadrbin Amennn.

    ReplyDelete