Saturday, January 17, 2015

ጥምቀተ ክርስቶስ

            ተ ስ           
                            እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን
በኢትዮዽያ  አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርዓት  መሰረት በየዓመቱ ጥር 11  ቀን በታላቅ ድምቀት የጥምቀት በዓል ይከበራል ለመሆኑ ጥምቀት ምን ማለት ነውእና በሌሎች በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን                                                                            
 ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መላ ሰውነትን በተቀደሰ ውኃ መነከር ወይም መዘፈቅ ውሰጥ ገብቶ መውጣት መነከር መውጣት መቀበር ማለት ነው አንድ ሰው በመጠመቁ ክርስቶስን በሞቱ ይመስለዋል ይኸውም ተጠማቂው ከቅዱሱ ውኃ ሲነከር በክርስቶስ ሞቶ ሲመስለው ከውኃ ሲወጣ ደግሞ ክርስቶስን በትንሣኤው ይመስለዋል፤ በዚህም ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናል፡
  እንግዲህ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሣ፤ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፡ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” እንዲል፡፡ /ሮሜ.፮፥፬ ቆላ ፥፲   
ጌታለምንተጠመቀ? 


   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጸድቅ አይል ጻድቅ፤ እከብር አይል ክቡር፣ እቀደስ አይል ቅዱስ የነገሥታት ንጉሥ፣ የኃያላን ኃያል፣ የአማልክት አምላክ፣ የቅዱሳን ቅዱስ (ቅድስናው የባሕሪው የሆነየአሸናፊዎች አሸናፊ፣ የባሕርይ አምላክ የሁሉ ጌታ ሲሆን፤ ለምን ተጠመቀ ቢሉ ሮሜ፱፥፭፣ ፩ዮሐ ፭፥፳፣ ፩ተሰ ፫፥፲፩፣ ቲቶ፪፥፲፩፣ ኢሳ ፱፥፮፣ ፩ጢሞ ፮፥፲፭፣ ራእይ ፲፱፥፲፩-፲፮/
፩ኛ. ለአብነት /ምሳሌለመሆን፡-
ጌታችን በዚህ ምድር በሥጋው ወራት የፈጸማቸው ትሩፋቶች ለኛ ምሳሌ ይኾነን ዘንድ ነው፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር በትሕትና ካጠበ በኃላ፥ “እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርሰ በእርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኃል፡ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሣሌ ሰጥቻችኋለሁና” ብሎ እንደ ተናገረ፡;ዮሐ፲፫፥፫ ይህንንም ቅዱሳን ሐዋርያት በትምህርታቸው መስክረዋል፡፡ ፩ዮሐ፪፥፮፣፩ጴጥ፪፥፳፩፣ዕብ፲፪፥፩፫ጌታችን ጾምን፣ ጸሎትን በተግባር ከነሥርዓቱ አስተማረን፤ በቃሉም አዘዘን “ባልዋጁባት ጣት የዘንዶ ጉድጓድ ይሰድዱባት” እንዲሉ፥ ጌታችን እርሱ ሳይፈጸም ትእዛዛቱን፣ ሕግጋቱን ፈጽሙ አላለንም፡፡ በተግባር ያሳየንን አዘዘን እንጂ፡፡የሃይማኖታችን ራስና ፈጻሚ” ተባለ ፡፡ ዕብ.፲፪፥፩፪ የሃይማኖታችንራስየሃይማኖታችን መሠረትማለት ሲሆን፤ ፈጻሚ ማለቱ፥ የክርስትና ሃይማኖት መሠረታዊ ሕግጋትን አድራጊ ማለት ነው፡፡
፪ኛ፡ጥምቀታችንን ሊባርክ /ሊቀድስ/ ለጥምቀታችን ኃይልን ሊሰጥ /ለመስጠት/
ከጥንት ጀምሮ እስከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጊዜ የነበረው የጥምቀት ሥርዓት ለአማናዊው የክርስቶስ ጥምቀት ምሣሌ ነበር፡ ከሥጋ ደዌና መቅሰፍት የሚዳንበት እንጂ፣ ልጅነትን የሚያሰጥ፣ መርገመ ሥጋንና ነፍስን ማራቅ የሚቻለው አልነበረም፡ ጌታችን ከተጠመቀልን በኃላ ግን፤ ተጠምቀን በሥጋ በነፍስ የምንከብርበት፣ ጸጋ ሥርየት ኃጢኣትንየምንጐናጸፍበትና፣ የመንግሥተ ሰማያት ዕጩዎች የምንሆንበትን ስጦታ የተቀበልንበት ነውና በዓላችን ብለን እናከብረዋለን፡፡ /ዮሐ ፩፥፳፮፣ የሐ/ሥራ ፲፥፴፬፴፱፣፲፱፥፩/
፫ኛ ምሥጢራትን ለመግለጽ፤ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ለዘመናት ተሠውሮ የነበረው የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር (ምሥጢረ ሥላሴገሃድ ኾኖ ተሰበከ፡ ይኸም ብቻ ሳይሆን የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት (የአብ ልጅ የድንግል ልጅየድንግል ልጅ የአብ ልጅ መሆኑበአብ በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት ዕለት ነውወልድ ክርስቶስ ተብሎ በአካለ ሥጋ አብ በደመና ኾኖ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ ምሣሌነት ሦስት አካላት በአንድ አምላክነት ተገለጹ፡ ክርስቶስ የተባለው የድንግል ልጅ እግዚአብሔር አብ ከባሕርይ የወለደው ስለመሆኑም፥ አንዱን ባሕርይ በተዋሕዶ “ልጄ” ብሎ በመጥራቱ፥ ሃይማኖት ታወቀ፤ ተረዳ፡ የቀናውን ኦርቶዶክስእምነት “ተዋሕዶ” ተብሎ የተጠራውም በዚህ መሠረትነት ነውማቴ ፫፥፲፫፲፯ ማር ፩፥፱ ፲፩ ሉቋ ፫፥፳፬፣ ዮሐ ፫፥፲፮-፲፰፣ ዕብ ፪፥፩-፫፣ኤር :-፲፮ የሐ/ሥራ ፲፫:-)
                    ጌታችን ለምን በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ?
፩ኛ፡ለካሣ ነው፡፡ካሣ ማለት ለተበደለ አካል የሚቀርብ የነፍስ ዋጋ ፈላማማለት ነው፡፡ ጌታችን በ፴ ዘመኑ የተጠመቀው፤ አዳም ከእግዚአብሔር በተፈጠረ በ፴ ዘመኑ ያገኘውን ልጅነት በዲያብሎስ በተሠወረበት በከይሲ በእባብምክር ተታሎ አስወስዶ ነበርና፤ እርሱም በ፴ ዘመኑ ተጠምቆ የዲያብሎስን ሥራ አጥፍቶ÷ ልጅነቱን ሊመልስለት በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ፡ በዚህም ዳግማዊ አዳም /ሁለተኛ አዳምተባለ፡፡ /፩ኛ ቆሮ፲፭፥፵፭፵፮/
፪ኛሕግን ለመሥራት ነው በብሉይ ኪዳን ለመንፈሳዊ አገልግሎትና ሕግ ለማድረስ የሚታጩበት  
የሚመረጡበትከ፴ ዓመታቸው ጀምሮ ነበር።ዘኁ፬፥፫፵፯ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የሕግ ባለቤት እንደመሆኑ፥ ማስተማር የጀመረው በ፴ ዕድሜው ነው፡ ሉቋ፫፥፳፩በዚህም መነሻነት በሐዲስ ኪዳን ሰዎች ለመንፈሣዊ ተግባር መመረጥ ያለባቸው በዕድሜያቸው ልክ ሙሉ ሲሆኑ፤ ኃላፊነት ለመሸከም በሚችሉበት የዕድሜ ልክ የዕውቀት፣ የብስለት ደረጃ ሲደርሱ መሆን እንዲገባው÷ ጌታችን በተግባር አሳየን፡፡
                  ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሄዶ ለምን ተጠመቀ ?
ጌታችን የዮሐንስ ጌታ፣ ፈጣሪ ነው፡፡ ዮሐንስ አስቀድሞም ሰለእርሱ ሲመሰክር፡- “አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል÷ ከእኔም በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኗል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው” ዮሐ ÷፳፱/“ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣሙ ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል” ማቴ፫፥፲፩/


 በማለት የክርስቶስን ቀዳማዊነት፣ ልዕልና መስክሯል፡፡ ወደ እርሱ ሊጠመቅ በመጣ ጊዜም “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህንብሎ ይከለክለው ነበር” ተብሎ ተጽፏል፡፡ /ማቴ ፫፥፲፬/

   ጌታችን የባሕርይ ጌታ /ፈጣሪሆኖ ሳለ፥ ስለምን ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተጠመቀ ቢሉ፡-

፩ኛስለትሕትናነው ጌታችን “ከእኔም ተማሩ  እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና” ማቴ፲፩፳፱ብሎ በቃል ያስተማረውን በተግባር ሲያሳየን፤ አገልጋዩ የኾነውን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ እኔ ይምጣ ሳይል፣ እርሱ ግን ቅዱስ ዮሐንስ ካለበት ድረስ ሄደ፡ ከእርሱ በላይ ካህን፣ መምህርጌታ፣ ንጉሥ ከወዴት አለምንም እንኳን ሰዎች ቢያከብሩንም ራሳችንን በትሕትና ማዋረድ እንዲገባን ጌታችን አስተማረን፡ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ አንተ በእኔ ልትጠመቅ አይገባህም እኔ በአንተ እንጂ ባለው ጊዜ ጌታችን አሁንስ ፍቀድልኝ እንጂ ጽድቅን/የነቢያት ትንቢትንመፈጸም ይገባናል አለው ተብሎ ተጽፏልና፡፡ (ማቴ፫፥፲፬)

፪ኛ፡ ሥርዓትን ለመሥራት 

ጌታችን እንደ ጌትነቱ ቅዱስ ዮሐንስ እርሱ ዘንድ መጥቶ እንዲያጠምቀው ቢያዘው ኖሮ፤ በየዘመኑ የሚነሡ ነገሥታት፣ ባለጠጎች ምእመናን አጥማቂ ካህናትን በቤተ መንግሥታችን፣ በእልፍኛችን መጥታችሁ አጥምቁን፤ ልጆቻችንንም አጥምቁልን ባሏቸው ነበር፡ ጌታችን ግን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ወዳለበት ባሕረ ዮርዳኖስ ሄዶ በመጠመቁ ምእመናን ካህናት ወደ ተሰየሙበት ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘንድ ሄደው እንዲጠመቁ ምክንያት ሆኖ ሥርዓትን ሠራልን  

              በጥምቀት ምን ጸጋ ይገኛል ?
ጥምቀት  የተፈጸመለት ተጠማቂ ልዩልዩ  ጸጋዎችን ያገኛል 
.ክርስቶስን እንለብሳለን  ሐዋርያው “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን

 ለብሳችሁታልና” /ገላ.፫፥፳፯ብሎ እንደተናገረ፡፡

በጥምቀት ከእግዚአብሔር በጸጋ እንወለዳለን፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “በስሙ ለሚያምኑት ለእርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይንም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም” ብሎ እንዳስተማረ፡፡ /ዮሐ.፩፥፲፩፲፭/

.በጥምቀት ድኅነትይገኛል ያለ  ጥምቀት   መዳን የለም “ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ /አምኖ

 ያልተጠመቀይፈረድበታል” ተብሎ እነደተጸፈ፡፡ /ማር.፲፮፥፲፮/

.ስርየኃጥያትንያሰጣል  በመጀመሪያይቱ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት

 ሦስት ሺህ ሰዎች አምነው “እንድን ዘንድ ምን እናድርግ ?” ቢሉት  “ንሥሐ ግቡ፥ ኃጢኣታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታን ትቀበላላችሁ” አላቸው፡ /የሐ/ሥራ ፪፴፷ከቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት በጥምቀት ኃጢኣት እንደሚሠረይ፣ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ መቀበል እንደሚቻል፣ መረዳት ይቻላል፡፡

 .የክርስቶ ደቀመዝሙር ያደርጋል   ጌታችን ቅዱሳን ሐዋርያትን ወንጌልን እንዲያስተምሩ ወደ ዓለም

ሲልካቸው “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥… ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸውሜቴ ፳፷፲፱ብሎ አዝዟቸዋል፡ እነርሱም በዚህ ትእዛዝ መሠረት ዓለምን ዙረው አስተምረው፤ አሳምነው፤ አጥምቀው፤ ሰዎችን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፤ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከክህደት ወደ ሃይማኖት፤ ከጥርጥር ወደ እምነት፤ መልሰዋል፡ ጥምቀት ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ለመመለሳችን ማረጋገጫ ማኀተም ነውና፡፡ /የሐ/ሥራ ፰፥፴፰ ፣፲፮፥፲፮፥፲፭፴፫
                                  ከተራ ምን ማለት ነው ?

ከተራ፡ ቃሉ እንደሚያመለክተው የሚፈስ ውኃ በአንዳች ነገር መዝጋት፣ ማቆም፣ መከልከል ማለት ሲሆን፤ በዓሉየጥምቀትውሃና ባሕሩንየሚከተርበት ዕለት መሆኑን ያለመከታል፡ ይህውም ጥር  ቀን የጥምቀት ዋዜማ ነውበዘመነ ኦሪት 


የእግዚአብሔር ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም ውኃው ቦታእንደሚከትርእንደሚከማችተነግሯቸው ነበር ይህም ተፈጽሟል፡፡ ኢያሱ ፫፥፲፫፲፮በሀገራችን ይህ በዓል ሲከበር ኖሯል፡ ኋላም በዘመነ ክርስትና ቤተክርስቲያን በምሥጢር አስማምታ በሐዲስ ሥርዓት ታክብራለችበዚህም ዕለት ታቦታት ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ተዘጋጀው ባሕረ ጥምቀት ይሻገራሉ፡ ይህም ጌታችን ከገሊላ ተነሥቶ ወደ ዮርዳኖስ መጓዙን የሚያስታውስ ሥርዓት ነው፡፡ /ማቴ፫፥፲፫  ማር.፩፥፱/
                           የጥምቀት ጾም/ጾመ ገሃድ
የጥምቀት ጾም የምንለው በከተራ በሚውልበት ቀን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሆኖ ጾመ ገሃድ በመባል የምንጾመው ሲሆን ይህም ከጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ጥምቀት በመሆኑ በዚህ ታላቅ በዓል በፍጹም ደስታ እንድናከብረው ስርዓተ ቤተክርስቲያን ስለሚያዝ የከተራ ዕለት  የገሃድ ጾም ይጾማል፡፡ የከተራ ዕለት ሰንበት ካልሆነ በቀር፤ ሁል ጊዜም ጾም ሆኖ ይውላል፡፡
በዓለ ጥምቀት - 

ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዘመኑ በእደ ዮሐንስ፣ በማየ ዮርዳኖስ በዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር ፲፩ ቀን እኩለ ሌሊት የተጠመቀበት ዕለት ነው፡ በዋዜማው በወንዝ ዳርበሰውሠራሽየውኃግድብበዳስ በድንኳንታቦቱ ካደረ በኋላ፤ ሌሊቱን ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደረስ አድሮ፤ 
ሥርዓተ ቅዳሴውም ይፈጸማል፡ ይህም የክርስቶስን የጥምቀት ጊዜን የሚያዘክር ነውበወንዙ ዳር በግድቡጸሎተ አኰቴት ተደርሶ፣ አራቱም ወንጌላት ከተነበበ በኋላ ውኃው ተባርኮ ለተሰበሰበው ሕዝብ ይረጫል፡ ይህም የተጠመቀውን ሕዝብ ድጋሚ ለማጥመቅ የተደረገ ሳይሆን ጌታችን ለኛ ብሎ ያሳየውን ትሕትና ለመመስከርና ከበረከተ ጥምቀቱ ምእመናን ለማሳተፍ የተደረገ ሥርዓት ነው፡፡
                          ቃና ዘገሊላ ምን ማለት ነው ?
ቃናዘገሊላበጥምቀት ማግስት በተጠራበት ቤት ውኃን የወይን ጠጅ ያደረገበት ተአምር የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ በወንጌል እንደተጻፈው “በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሠርግ ነበር
እንዳለ፡ ጌታችን በጥር ፲፩ ሌሊት እንደተጠመቀ ልዋል ልደር ሳይል ዕለቱን ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄዶ  መዓልትና ሌሊት ጾሞ ከገዳምሲወጣ ቀኑ የካቲት  ይሆናል፡ በሦስተኛ ቀን የተባለውም ከገዳም ከወጣ በኋላ ያለው ተቆጥሮ ነው ቀኑም የካቲት ፳፫ ቀን ይሆናል፡ የቃና ዘገሊላ በዓል ዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውልና ለማክበር ስለማይመች የውኃን በዓል ከውኃ ጋር ቢያከብሩት ይስማማልና በማለት ከጥምቀቱ ጋር አስጠግታ ቅድስት ቤተክርስቲያን 
ጥር12ቀንታከብራለ(ዮሐ፪፩፲፩)እኛም በዚህች በጸናች በጎላች በተረዳች በንጽሕትተዋሕዶ ሃይማኖታችንና ምግባራችን ጸንተን የክብሩ ወራሾች እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት  የድንግል እናቱ ጸሎት  የጻድቁ አባታችን ተክለሃይማኖት አማላጅነት አይለየንአሜን፡፡
                    


No comments:

Post a Comment