ተራዳሂው መልአክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና ስርዓት መሰረት በየዓመቱ ሰኔ 12 ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያውን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን ይህም ዕለት አስደናቂው የእግዚአብሔር ቸርነት፤ በመልአኩበቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት የተፈጸሙ ተአምራት እያስብን ሁሉን ማድረግ የሚችለውን፤ አምላክ እናመሰግናለን ።
ቅዱስሚካኤል የሚለው ስም ቅዱስ እና ሚካኤል የሚባሉ የሁለት ቃላት ውህድ ነው፡;
ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው።ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። ዘጸ 15፥11። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ 85፥8።
በዚህ ዕለት በኪልቂያ መስፍን የነበረ አስታረኒቆስ የሚባል ደግሰው ሚስቱ አፎሚያ የምትባል ሴት ነበረች ሁለቱም ሃይማኖታቸው የጸና በምግባር የከበሩ እግዚአቤሔር ለቅዱሳን የገባውን ቃልኪዳን በማሰብ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክርበመዘከርመታሰቢያውን እያደረጉይኖሩነበር።በኃላም
አስተራኒቆስ ታሞ ሞተ ቅድስት አፎሚያም ሃብት ንብረቷን ለድሃ ለችግረኞች እየመጸወተች ዝክር እየዘከረች ሳለ የበጎ ነገር ጠላት ስይጣን በክፋት ተነሳባት በተከበሩ መነኮሳትእና በአረጋዊ ተመስሎ ከተቀደሰው አገልግሎት ለመለየት መጣ የክፋት ትምህርቱ እናታችን ሔዋን እንዳስናከላትዘፍ3፥1-11 እሷንም ጾም ጸሎትማብዛት ያለጊዜእንደሚያስቀስፍ፣ ትዳርይዛ እንድትኖር፣ሃብትንብረቷን እየመጸወተች እንዳታባክን፣ሰበካት ቅድስት አፎሚያም አባቴ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግንክፉነውአትጹሚ አትጸልይ ያልከኝ ጌታ ምጽዋትን ከመስዋዕት አትለይ ብሎ የለምን፣ሁለተኝስ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው እርግብ እንኳን ባሏ ከሞተባትከሌላለ ወንድ አትቀርብም ፡ታዲያ ጥንቱን በንጽህና ሊኖር የተፈጠረው ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳፍዳ ሊሆንበት ነው?ብላ ባሏ ታሞ ሳለ ያሳለላትን ስዕለ ሚካኤልን አምጥታ ብታሳየው<< ሰኔ 12ቀን መጥቼ ከተመካሽበት ከዚህ ስዕል ጋር አጠፋሻለው>> እያለ እንደ ጢስ ተኖ ጠፋ።በመጽሐፍ ቅዱሳን በጥላቸው ይፈውሱ ነበር እንደተባለ ቅድስት አፎሚያም በመልአኩ አማላጅነት በመታመኗ ከጠላቷ ከዲቢሎስ እጅ እንደዳነች እንመለከታለን ዘፍ.48:16 “ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ።”ሲል ታላቁ አባት ያዕቆብ በችግሩ ጊዜ እንደረዳው መሰክሯል።ሰይጣንም ተንኮሎ ከተጋለጠበት በኃላ ዳግመኛ ሰኔ 12ቀን በነግህ ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጥቶ ጾም ጸሎትሽ ፣ስግደት ምጽዋትሽ፣ዐርጎልሻል፣ያስሁት ሚካኤል በዚያ ቀን ቅድመ እግዚአቤሔር ይቆማል እና<< መጥቼ አጠፋሻለው እንዳለሽ >>አውቄ ላድንሽ መጥቻለሁና ስገጅልኝ አላት፤ አንተ ማን ነህ ? አለችው ፣እሱም ሊቀመላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነኝ አላት ።ቅድስት አፎሚያም የንጉስ መልከተኛ ያለማኅተም ይፈርዳልን?በትረ መስቀልህ ወዴት አለ?አለችው መስቀል አሲዞ መሳል ልማድ ነው እንጂ እኛስ አንይዝም አላት፤ቅድስትአፎሚያም ቆየኝ ስዕሉን ላምጣልህ ብላ ዘወር ስትል አርያውን ለውጦ ደብረ ጽልመት መስሎ አነቃት ያን ፤ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደ ዓይን ጥቅሻ ፈጥኖ ደርሶ ቀጥቶ ፣አምሎ፣ ገዝቶ እመቀመቃት ጥሎታል ዘጸ.23:20-21 “በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።>> ሲል ቅዱሳን መላእክትን እንድናከበር በመታዘዙ ቅድስት አፎሚያም ይህን ቃል አክብራ ክብር ለሚገባው ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብር ሰጥታ ዝክሩን ብታዘክር ሰዕሉንም አክብራ ስለያዘችው በስዕሉ ባለቤት በቅዱስ ሚካኤል ጸጋ በመታመኗ ከሳሿ፤ ዲያቢሎሰን ፤ድል አድርጋለች በመጽሐፍም ዳን6፤22“በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፥ ንጉሥ ሆይ፥ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።”እንዲል አንበሳው ዲያቢሎስን በፍጹም ሃይማኖት ድል ለመንሳት የበቃችው በቅዱስ ሚኬኤል አማላጅነት እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል። ሰይጣን እና ሠራዊቱ፤‹‹የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት››፤የተዋረዱ፣የወደቁ፣ወደ ጥልቅ የተጣሉ ናቸው። ‹‹ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት››፣ ‹‹… የቀደመው እባብ ተጣለ:: ወደ ምድር ተጣለ:: መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ፡፡›› (ይሁቁ.6፤ 2ጴጥ2.4፤ ራእ12.9) በቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ጸሎት ከጠላት እጅ ነጻ ከወጣች በኃላ ሃብት ንብረቷን በሙሉ ለቅድሰት ቤክ እና ለነዳያን አከፋፍላ በሰኔ 12 ቀን በክብር ዐርፋለች ስዕሉም ከእቅፉ ወጥቶበሮበሮ ከቅድሰት ቤ/ክ ያለምንም መስቀያ ተሰቅሎ ተገኝቷል ኃላም አብቦ አፍርቶ በአበባው በፍሬው ብዙዋችን የሚፈውስ ሆኗል።
እንዲሁም በዚህ ዕለት የባህራንንም የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት ቀይሮ በልቅሶው ፈንታ ሠርጉ እንዲከናወን ያደረገበት ቀን ነው። በዚህም የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸዋል ተብሎ የተጻፈው ቃል በተግባር ተገለጠበት መዝ 33:7 ቅዱስ ሚካኤል ለቅድስት አፎምያ እና ለባህራን ብቻ ሳይሆን ስለ ሙሴ ሥጋም ዲያብልስን የገሠጸ ያሳፈረ ኃያል ገናና መልአክ ነው ይሁዳ 1:9 ቅዱስ ሚካኤል ይታደጋል ይራዳል ዳን.9:22 “(የእግዚአብሄርም መልአክ) አስተማረኝም፥ ተናገረኝም እንዲህም አለ። ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ። ሲል ምሥጢርን ሊገልጽለት እንደመጣ ይናገራል እንዲሁም በዳን.10:21 “ ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።” ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ሲል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ክብር አልቆ ያሳያል አንድም ሊራዳ የሚመጣ ተራዳይ መልአክ መሆኑን ያሳያል። ዕብ.1:14 “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” የእግዚአብሔርን ቸርነት ወደ ሰው ልጆች የሰው ልጆችን ምልጃእና ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያሳርጉ እንደሆነ እና በአማላጅነታቸው የሰው ልጆችን ወደ ድኅነት የሚያደርሱ ናቸው ። ዳን.12:1 “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነጀምሮእስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።” ቅዱስ ሚካኤል በዕለተ ምጽዓትም ስለ ምዕመናን ይቆማል ከሳሻቸው ሰይጣንንም ተበቅሎ ይቀጣዋል በዚያን ጊዜ ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል መባሉም ለዚህ ነው ።ስለዚህ እኛ በመልአኩ ስም ዝክር እየዘከርን መታሰቢያ እያደረግን የመልአኩን ያማላጅነት ጸጋ እንጠቀማለን። እነሱንም ባከበርን ጊዜ የፈጠራቸውን ቅዱሳን መላእክትን የሚያጸናቸውን እግዚአቤሔርን ማክበራችን እንደሆነ ሲናገር“እግዚአብሄር የቀደሰውን ክቡር ብትለው ከንቱ ነገርን ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረውበዚያን ጊዜ በእግዚአብሄር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ”ኢሳ58፡13ስለሚልቅዱሳን መላእክትንብናከብራቸው የበረከት ተሳታፊዎች እንሆናለንቅድስት አፎሚያን እና ባሕራንን ከሞት ያዳነ የምህረት መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የሚፈታታነንን ጠላታችንን ዲያቢሎስን ከእግራችን በታች ይጣልልን እንደ ባህራንም መራራ ህይወታችንን በአማላጅነቱ እንዲያጣፍጥልን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡
ማሳሰቢያ የተከበራችሁ አንባብያን በሚቀጥሉት ዝግጅቶቻችን የ ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸውን ፤አማላጅነታቸውን፤ጸጋቸውን ፤ክብራቸውን ፤በአጠቃላይ በቅዱሳን መላእከት ዙሪያ ቅድሰት ቤተክርስቲያን ያላትን አስተምሮ እና መናፍቃን ስለቅዱሳን መላእክት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ለመዳሰስ እንሞክራለን እንትከታተሉ እንጋብዛለን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ደንግል
ወለማስቀሉ ክቡር ይቆየን
“በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክንበፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።>>
ReplyDelete