ጥምቀተ ክርስቶስ
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን
በኢትዮዽያ አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርዓት መሰረት በየዓመቱ ጥር 11 ቀን በታላቅ ድምቀት የጥምቀት በዓል ይከበራል ለመሆኑ ጥምቀት ምን ማለት ነው ? እና በሌሎች በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን
ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መላ ሰውነትን በተቀደሰ ውኃ መነከር ወይም መዘፈቅ ውሰጥ ገብቶ መውጣት መነከር መውጣት መቀበር ማለት ነው አንድ ሰው በመጠመቁ ክርስቶስን በሞቱ ይመስለዋል ይኸውም ተጠማቂው ከቅዱሱ ውኃ ሲነከር በክርስቶስ ሞቶ ሲመስለው ከውኃ ሲወጣ ደግሞ ክርስቶስን በትንሣኤው ይመስለዋል፤ በዚህም ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናል፡