Wednesday, June 13, 2012

ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?

ክፍል አምስት ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?
            ከዚህ ቀደም ተከታታይ ባቀረብናቸው ጽሑፎች ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደማይመለከታት ከብዙ በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል ቀጣዩን ጽሑፋችንን ይዘንላችሁ ቀርበናል በአሰተውሎት ማንበቡን እግዚአብሔር ያድለንበክፍል አራት  ጽሑፋችን«ወለደት ድንግል ዘፀንሰቶ እንዘ  ኢተአምር ብእሴ በስጋ ዘፈጠሮ   ለርእሱ ወወለደቶ ዘእንበለ ደነስ ወሕማም ወኢረሰስሐት በሐሪስ ሐፀነቶ ዘእንበለ ፃማ ወድካም ወአጥበቶ ዘእንበለ ድካም ወአልሐቀቶ በሕግ ዘሥጋ  ዘእንበለ  ትካዝ ።»
 « ለተዋሕዶ የፈጠረውን ሥጋ ያለ ወንድ ዘር ያለ ኃጢአት ያለምጥ ወለደችው  የአራስነት ግብርም አላገኛትም ያለድካም ያለመታከት አሳደገችው ያለድካም አጠባችው  ለስጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላው ምን አለብሰው ሳትል አሳደገችው» ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ ፳፰፡፲፱ትርጉም  ማብራሪያውን በቀጣዩ ጽሁፋችን እንመለከታለን ብለን ነበር ያቆምነውሐዋርያዊው ቅዱስ አትናትዮስ ካስተማረው ትምህርት እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት በሚገባ ማስተዋል ይቻላል ግልጽ   ለማድረግም የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ይቻላል
 1.ያለ ኃጢአት ከሚለውቃልወላዲተ አምላክ ጌታን ምንም ምን ኃጢአት ሳያገኛት እንደወለደችው ያስረዳናል      
2.ያለምጥ የአራስነት ግብርም ሳያገኛት ከሚለው ደግሞ ሌሎች ሴቶች በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት በምጥ በአራስነት የሚወልዱ ሲሆን እረሷ ግን ከመርገመ ከእዳ ከበደል የተለየች በመሆኗ ምጥና አራስነት አልነበረባትምይህምከመላአኩየምስጋና ንግግር ተስማሚነትያለውነውቅዱስ ገብርኤልሲያበስራትከላይ ከተጠቀሱትየመርገምምልክቶችእመቤታችን የተለየች መሆኗን ሲያስረዳ«አንች ከሴቶት መካከል የተባረክሽ ነሽ » ሉቃ 1 ፡ 28 በማለት  አመሰግኖአታል።ለመሆኑ እርሷ በሌሎች ሴቶች ያለ የመርገም ፍዳ ካለባት ከሌሎች ሴቶች መለየቷ ምን ላይ ሊሆን ነው ?ስለዚህ እመቤታችን የመርገም ፍዳ ይመለከታታል በሎ ማስተማር ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ የራቀ ትምህርት ነው ማለት ነው ። ውላዲተ አምላክ የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ቅዱስ አትናትዮስ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቅዱሳን አበውም መስከረዋል  ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድንግል ማርያም የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ስያስረዳ እንዲህ በማለት በሚደንቅ ንግግር እንዲህ ይላል « ከመገባሪ ጠቢብ ሶበ ይረክብ ግብሮ ዘይትጌበር ይገብር እምኔሁ ንዋየ ሰናየ ከመዝ እግዚእነ ሶበ ረከበ ሥጋሃ ቅዱስ ለዛቲ ድንግል ወነፍሳ ቅድስት ፈጠረ ሎቱ መቅደስ ዘቦቱ ነፍስ » ሃይ አበ ዘአፈወርቅ 66 ፡14ትርጉም « ጥበበኛ ንጹህ አፈር ባገኘ ጊዜ ጥሩ እቃ እንደሚሰራበት ጌታችንም የድንግልን ንጹህ ሥጋዋን  ንጹህ ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ይዋሃደው ዘንድ ነፍስ ያለውን መቅደስ ሰውነቱን ፈጠረ » መቼም የቀናች የተረዳች ርትዕት የሆነች የተዋህዶ ምዕመን ሆኖ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የማያውቅ አለ ማለት ይከብዳል ምንም በማያሻማና ግሩም በሆነ አገላለጽ ሊቁ እነዳስቀመጠልን አምላክ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነው ምንም ምን እንከን ከሌለው ሰውነቷ ነው  ሊቁ የእመቤታችንን ነፍስና ሰጋዋን በንጹሕ አፈር መስሎታል በዚህ አገላለጹ ከሰው ወገን ተመርጣ ለአምላክ እናትነት የበቃች መሆኗን አስረዳን ምክንያቱም የሰው ሁሉ ተፈጥሮው ከአፈር ነውና ። ወላዲተ አምላክ እንደሰው ሁሉ ተፈጥሮዋ ከአፈር ቢሆንም ቅሉ ሊቁ እንደተናገረው « ንጹሕ አፈር » የሚለው አገላለጽ በሰዎች ከደረሰ አዳማዊ መርገም የተለየች መሆኗን ያስረዳናል ቅዱስ ኤፍሬምም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ዘር ያልተዘራባት እርሻ በማለት በንጹሕ እረሻ መስሎአታል ልበ አምላክ ዳዊትም« እንደ ዝናብ በንጹሕ እርሻ ላይ …….. ይወርዳል »  መዝ 71 ፡6 በማለት ጌታን በዝናበ ሕይወት እመቤታችንን ደግሞ አረም ተዋስያን በሌሉት ንጹሕ መሬት መስሎ ትንቢት ተናግሮአል ይህም ምንም ተፈጥሮዋ ከሰው ወገን ብትሆንም የኃጢአት አረም ህዋስ ያልነካት ንጽህት ዘር መሆኗን ያስረዳናል  ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በንጹሕ አፈር የመሰላት ። ሊቁ በመቀጠልም « ንጹሕ ስጋዋን ንጹሕ ነፍሷን  ባገኘ ጊዜ » በማለት የወላዲተ አምላክ ነፍሷ ስጋዋ ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ ንጹሕ ቅዱስ መሆኑን ይመሰክራል ባገኘ ጊዜ አለ እንጂ ሊዋሐደው ሲል አነጻው አላለም ሰለዚህም እውነተኞች ቅዱሳን አበው በጥንቃቄ የመሰከሩትን የእመቤታችንን ንሕጽና ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊያስተባብል አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን « እኛ ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን » ገላ 1 ፡ 8 ባለው መሰረት ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊሽረው ወይም ሊለውጠው አይችልም ቢሞክር እንኩአን የተለየ የተረገመ ነው ቅድስት ቤተክርስትያን የምትመራው ቀደምት ቅዱሳን ባስተማሩን እውነተኛ ትምህርት እንጂ አዲስ ዛሬ የሚፈጠር ምንም የለም ስለዚህ ከአንዳንድ የዘመናችን ሰዎች የተሳሳተ ትምህርት ብንሰማ እነሱ የተለዩ ይሆናሉ እንጂ የሰማይ መልአክ ነኝ የሚል ቢመጣ እንኳን የቤተክርስትያን አስተምሮ አይለወጥም  
  ይቆይን 

2 comments: