Tuesday, April 3, 2012

ኪዳነምሕረት

           በስመአብ ወወለድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
                         ኪዳነምሕረት የምሕረት አማላጅ 
         በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን በታላቅ ድምቀት የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል ።   በዓሉም ታለቅነት እንደምንድ ነው ቢሉ የኃጥአን ተስፋ የደካሞች ምርኩዝ ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከአኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን እና የቃል ኪዳን ፍጻሜ የተከናወነበት ዕለት ሰለሆነ ርዕሰ ኪዳናት ይባላል።ድንግል ማርያምም የኪዳናት መደምደሚያ ናተ እና እርሷም ኪዳነምሕረት ትባላለች ።
              በቅዱሳት መጻሀፍት ታሪክ እንደምንማረው በብለይኪዳን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከቅዱሳንወዳጆቹ የፈጸማቸው አምሰት ልዩልዩ ኪዳናት ተከናውነዋል እነዚህም

ኪዳናት የራሳቸው አስደናቂ ባህሪያት የነበሯቸው እና በኃላ ዘመን ለሚፈጸመው አማናዊው ውል መርገፍ ምሳሌ ነበሩ።የኪዳናቱም ባለቤት የሠራዊትጌታ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ለቅዱሳኑ
የገባው የተማማለው ውል(ስምምነት) ቃል ኪዳን ይባላል።
                                     ቃል ኪዳን
          ቃል ኪዳን የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በሐዲስ ኪዳንለ33ጊዜያህልተጠቅሷል  >ተካየደ ተማማለ ቃል ተገባባ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን > የሚለው ጋር ሲያያዝ> ይባላልትርጉሙም< ውል ስምምነት >ማለት ነው።ስለዚህ
      በብሉይ ኪዳን የተፈጸመት ኪዳናት የቆዩ ውሎች ስምምነቶች ይባላሉ፤ምክንያቱም ኪዳናቱ የተፈጸሙበት ዘመናት ርዝመተ እና በዓመተ ፍዳ የተፈጸሙ ስለሆኑ የመከራውን ጊዜ ያወሳሉ፤ በሐዲስ ኪዳንም የተፈጸሙ ኪዳናት ሐዲሱ ውል ከተፈጸመ በኃላ የተከናወኑ ስለሆኑ ዘመነ ምህረትን የሚያውጁ ጸጋቸው የበዛ አማናዊ ኪዳናት ናቸው።ቃልኪዳን ሲፈጸም የቃልኪዳኑ ባለቤት እና ቃልኪዳኑን በሚቀበለው መካካል መሐላቸውን ስምምነታቸውን ለማጽናት ምልከትን ማኖር የተለመደ ሥርዓት ነው።
                                  ኪዳነ አዳም
       በብሉይ ኪዳን ከተከናወኑት ኩዳናት የመጀመረያው በአዳም እና በእግዚአብሔር መካካል የተደረገ ሲሆን፤ ምልከቱም እጸ በለስ ነው ሰምምነቱም ቀዳማይ ሰው አዳም ከፈጣሪው የተሰጠውን ትህዛዝ ቢጠብቅ በህይወት እንደሚኖር ባይጠብቃት ግን የሞት ሞት እንደሚሞት ነገረው እርሱም ለ7 ዓመታት ሕግን ስለጠብቃት በፍጹም ክብር ይኖር ነበር። በኃላ ግን ሕግን በመጣሱ ምክንያት ቃልኪዳኑን ስላፈረሰ ሞት ተፈረደበት በዚህም እያዘነ ፈጣሪውን ይቅርታ ቢጠይቅ ከአምስተ ቀን ተኩል በኃላ ከልጅልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው የምህረት ተስፋን ሰጠው።ዘመኑም ሲደርስ የአዳም ተስፋ ከሆነች ከቅድስተ ቅዱሳን ከድንግል ማርያም እግዚአብሔር ወልድ በቤተልሔም ተወለደ ዓለሙንም አዳነ ።
                                 ኪዳነ ኖኅ ኖኅ
   ኃጢአታቸው እጅግ በበዛ እና በረከሱ ሰዎች መካካል የነበረ ንጹሕ እና ጸድቅ የነበረ ሰው ነው፡፡ ፍጥረቱ በሙሉ ቢበድሉም እግዚአብሔርም  ሰውን በመፍጠሩ ቢጸጸትም ሰብአ ትካት መመለስ ባለመቻላቸው አምላካዊ ፍርዱን ግን አልተወም ምድርንም በንፍር ውኃ አጠፋት ዘፍ6፥18። ጻድቁ ኖኅ ግን ስምንት ነፍስ ይዞ ከመዓቱ ቢያተርፈው ለእግዚአብሔር መሠዋያን ሠራ መሥዋዕትን አቀረበ  እግዚአብሔርም  የኖኅን መሥዋዕት በመቀበል ቃልኪዳንን ፈጸመ ውሉም >ዘፍ9፥8-17 ምደርቱንም ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንደማያጠፋት በስሙ ማለለት ይህም እስከዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።
                                ኪዳነ አበርሃም
          አብርሃም አባታችን ከሚኖርበት ሀገሩን ቤተሰቡን ትቶ እንዲወጣ  ከእግዚአብሔር ቢታዘዝ እርሱም ፈቃደኛ በመሆን ወደ ማያውቀው ሀገር ሲሰደድ በልቡ የታመነው ከአምለኩ የተቀበለው የተስፋ ቃልኪዳን ይዞ ነበር። የቃል ኪዳን ምልክቱምቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላላም ቃል ኪዳን ይሆናል ።>>በማለት አብርሃምን ከወገኖቹ ጋር የእግዚአብሔር ሕዝብ ለርስቱ የተለየ የተመረጠ እንዲሆኑ አድርጓል።
                                   ኪዳነ ሙሴ
         ኪዳነ ሙሴ ይህ ኪዳን ለሊቀ ነቢያት ሙሴ የተሰጠ ሲሆን  ሕዝቡትዕዛዘ እግዚአብሔርን እንዲጠብቁ እና ከእርሱ ሌላ አምላክ እናዳያመልኩ መመሪያ ይሆናቸው ዘንድ በነብዪ አማካኝነት የመጀመሪያቱን ጽላት በመስጠት ቃል ኪዳኑን  አጽንቷል ።ይህም ለዘለዓም ሥርዓት ሆኖ ይኖራል ሕዝቡም ታቦተ ጽዮንን ባከበሯት ጊዜ በረከተ እግዚአበሔር ይበዛላቸው ነበር። የኪዳኑም ምልክት ታቦተ ጽዮን ነበረች ለእሰራኤል  ዘነፍስ ክርስቲኖችም ምህረት የምታሰጥ አማናዊት ታቦት ዘዶር ድንግልማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘናት የቃልኪዳን ምልከታችን ኪዳነ ምሕረት ናት ።ዘጸ24፥1-20
                                       ኪዳነ ዳዊት
          ይህ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ከተፈጸሙት ዐበይት ኪዳናት አንዱ ሲሆን ከእረኝነት አንስቶ የመረጠው እግዚአብሔር በታናሽነቱ እዝበ  እስራኤልን ይመራ ዘንድ የመረጠው በትረ መንግሥትን ከቤቱ ለዘላዓለም እንዳማይጠፋ ቃል ኪዳን ገብቶለታል መዝ131፥11-13 ትዕዛዙን ለሚጠብቁት በሙሉ መሐላውን ሲፈጽምላቸውእንደሚኖር አረጋግጦለታል ።የዚህ መሐላ ምልክቱ በትረመንግሰት ሲሆን የይሁዳ አንበሳ ከርስቶስ የዳዊት ዘር ከሆነች ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በእስራኤል ዘነፍስ ለመንገሱ ምሳሌ።ዳዊትበመናገሻው ከተማ በጽዮን እንደነገሰባት የዓለም ንጉሥ ክርስቶስም በመናገሻ ከተማው በደብረ ጽዮን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅጸን ለመንገሱ ምሳሌ ነው።
          እንግዲህ ከላይ የተመለከትናቸው ኪዳናት በሙሉ የእግዚአብሔር ምሕረት የተገለጠባቸው የቅዱሳኑ ጸጋ የታየባቸው ደኅነተ ሥጋን ብቻ ያሰጡ የነበሩ ቃልኪዳናት ነበሩ።
          አማናዊው እና እውነተኛው ኪዳን ሲደርስ የአባቶችን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ ጠላቶቹ ሳለን ወዳጆቹ ያደርግን ዘንድ የጥልን ግድግዳአፍርሶየምሕረትንጸጋአበዛልን፣በከበረደሙፈሳሽነትህይወትንአደለን።ዳግማዊአዳምክርስቶስምከዳግማዊት ሔዋንከኪዳነምሕረትተወልዶሰላማችንንአወጀልንፍኖተጽድቅንምአቀናልን።ጠፍተንእንዳንቀርምለርስቱየመረጣቸውን፣የወደዳቸውን፣ያከበራቸውን ፣ያጸደቃቸውን፣ ቅዱሳንን ለእኛ ተስፋ እንዲሆኑ የማይጠፋ መሐላንም ሰጣቸው ።
    የቀደሙት አባቶቻችን የልባቸው ማረፊያ ትሆን ዘንድ ወልድ በተለየ አካሉ ማደሪያው ያደረጋት መቅደሰ ሰሎሞን፣ የአዳም ተስፋው፣ የኖህ መርከቡ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ የሙሴ ጽላት ፣የዳዊት በገና፣ የኢሳይስ ድንግል ታቦት  ዘዶር ድንግል ማርያምም የምህረት ቃልኪዳንን የካቲት16 ቀን ተቀብላለች ይህም ቃልኪዳን የተለየ የምሕረት ቃልኪዳን ነው።ከፍጡራን መካከል እንደእርሷ የተለየ ቃል ኪዳንን የተቀበለ የለም፤ ወደፊትም አይኖርም፣እርሷ ከሁሉም ተለይታ የከበረች ምልዕተ ጸጋ ስለሆነች የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ታሳርጋለች በተሰጣት ጸጋም ለዘለዓለም ስታማልድ ስታስምር ትኖራለች ።
      በዚህ መሰረት ኪዳምህረት፣ ድንግልማርያም፣ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በመካነ ጎሎጎታ በተቀበለችው የምህረት ቃልኪዳን ከተፈጸማላቸው ተስፈኞች መካከል አንዱ ስምዖን የሚባል ደግሰው ነበር እንግዳ ተቀባይ ስለነበር በዚህ ምግባሩ ሰይጣን ቀናበት እንግዳ መሰሎ ከቤቱ መጣ ስምዖንም ምግብ አዘጋጅቶ አቀረበለት ይህን አልበላም አለ ።ሙኩት አርዶ አሰናድቶ አቀረበለት ።ይህም አይስማማኝም አለው እንኪያስ ምን ላምጣልህ አለው ።ልጅህን አርደህ አሰናድተህ ብታመጣልኝ እበላለው አለው።ለጊዜው አዘነ ኃላ ግን አብርሃም ክብር ማግኘት ልጁን ሰጥቶ አይደለምን የእግዚአብሔር እንግዳ ማሳዘን አይገባኝም ብሎ ልጁን አርዶ አሰናድቶ ሰጠው ቅመስልኝ አለው ።አይሆንም አለ ግድ ቢለው ጥፍሩን አስነክቶ ቀመሰለት ከመረቁ ጋር ተዋህዷታል ያን ቢያጣጥመው ቢጣፍጠው ያቀረበውን ጥርግ አድረጎ በለ ።ከዚህ በኃላ እህል የማይቀምስ ሆነ ቤተሰቦቹን ጨርሶ ጐረቤቶቹን፣ጐረቤቶቹን ጨርሶ መንገኞችን እየያዘ ሲበላ ሰባ ሰምንት ሰውበላ።የማይታወቅበት ሲሆን ሸሽቶ ወደ ሌላ ሀገር ሄደ ከመንገድ ቢየደባ የማያገኝ ሆነ ተነስቶ ሲሄድ አንድ ነዳይ ከመንገድ ተቀምጦ አየ ሊበላው ቢሄድ ሰውነቱ ከቁስል ነዶ አይቶ ተጸየፈው ውኃ በመንቅል ይዞ ነበር ነዳዪም በሥላሴ  አለው ዝም አለው።በሚካኤል በገበርኤል አለው። ዝም አለው በድንግል ማርያም አለው ይህችስ እንደምታድን በልጅነት ሰምቻለው ብሎ መንቀሉን ሰጠው ።ንቃቃቱ እንዃን ስይርስለት ጨረስህበኝ ብሎ ነጥቆት ሄደ።ከዚያም ከዋሻ ገብቶ ሞተ መላእክተ ጽልመት ነፍሱን እጅ አድርገው ሊያስፈርዱ ከጌታፊት ቀረቡ፤ እመቤታችን ልጄ ሆይ ይህቺን ነፍስ ማርልኝ አለችው ጌታም ሰባሰምንት ነፍስ ያጠፋ ፈጣሪውን የካደ ውሻ ይማራልን?አላት በስሜ የተጠማ አጠጥቶ አይደለምን አለችው እንኪያስ ይመዘን አለ።ቢመዘን ሰባስምንት ነፍስ የሚመዝን ቢሆን እመቤታችን በጥርኝ ውኃ ጥላዋን ጣል አድርጋበት ያች ጥርኝ ውኃ መዝናለች መላእክተ ጽልመትም እርሷ እያለች ምን እናገኛለን ብለው አፍረው ተመለሱ ።ያቺንም ነፍስ መላእክተ ብርሃን በዕልልታ ወደገነት አስገብተዋታል።
              የቀደሙት አባቶቻችን የልባቸው ማረፊያ ትሆን ዘንድ ወልድ በተለየ አካሉ ማደሪያው ያደረጋት መቅደሰ ሰሎሞን፣ የአዳም ተስፋው፣ የኖህ መርከቡ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ የሙሴ ጽላት ፣የዳዊት በገና፣ የኢሳይስ ድንግል ታቦት  ዘዶር ድንግል ማርያምም የምህረት ቃልኪዳንን የካቲት16 ቀን ተቀብላለች ይህም ቃልኪዳን የተለየ የምሕረት ቃልኪዳን ነው።ከፍጡራን መካከል እንደእርሷ የተለየ ቃል ኪዳንን የተቀበለ የለም፤ ወደፊትም አይኖርም፣እርሷ ከሁሉም ተለይታ የከበረች ምልዕተ ጸጋ ስለሆነች የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ታሳርጋለች በተሰጣት ጸጋም ለዘለዓለም ስታማልድ ስታስምር ትኖራለች
     
         ከበላዔሰብ (ስምዖን ) ታሪክ እንደምንማረው  ቸርነት ያባህሪ ገንዘቡ የሆነ የሰራዊት ጌታ እግአብሔር ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በሰጣት ቃል ኪዳን መሰረት አትግደል የሚለውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ያፈረሰውን ሰው የእርሷ አስዳነቂ ልመና እና የማይታበለው የልጇ የኢየሱስ ከርስቶስ ችርነት ታክሎበት ከሞት እንደዳነ እንመለከታለን ።ይህ ታሪክ በዕለተ አርብ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስረቶስ በስተቀኝ ተሰቅሎ የነበረው ፋያታዊ ዘየማን በህይወት ዘመኑ ሁሉ በበደል እና በእርኩሰት እንዲሁም ነፍስ በማጥፋት የታወቀ ሲሆን በበደሉም ምክንያት ሞት ተፈርዶበት በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ በአጠገቡ የተሰቀለው ያለምንም በደል እንደሆነ እና አምላክነቱን በሚሰራው ታምራት ከተረዳ በኃላ ኣብቱ በመንግሰትህ አስበኝ በማለት ይቅርታን በለመነ ጊዜ ቸርነቱ የማይቅበት አምላክ እውነት እልሃለው ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ በማለት የሞት ሰለባ የነበረውን  ሰው ለ5500 ዓመት ያህል በእሳት ነበልባል ትጠበቅ የነበረቸውን ገነትን ከተስፈኞቹ ተቀድሞ የገነት  በር ከፋች ለመሆን በቅቷል
    ኪዳነምሕረት ስንል የምሕረት ውል ሰምምነት ማለት ሰለሆነ ድንግል ማርያምም  በቀደመ ልመናዋ ለምና የምታስምር እንደሆነች እንረዳልን ።እመቤታችን ዝክሯን ለሚዘክሩ መታሰቢያዋን ለሚደርጉ ታምሯን  ለሚሰሙ፥ ለሚያሰሙ፥ ለሚተረገሙ ፥ውዳስዋን ለሚያደርሱ ፣ቅዳሴዋን ለሚቀድሱ ቤተ መቅደሷን ለሚሰሩ ፣በአጠቃላይ ሰሟን ለሚጠሩ ፈጥና የምትደርስ አፍጣኒተ ረድሔት ናት ።
             ከከበሩት ይልቅ የከበረች ናት እና እነከብራታለን ከፍ ከፍ እናደርጋታለን ስሟ ጠርተን አንጠግብም እና  ደጋግመን እናወድሳታለን ከጥፋት ውኃ የዳንባት የመዳናችን አርማችን ምልክታችን የመዳችን ትምክህት  ሰለሆነች እንደ ልጇ ዳዊት እምነ ጽዮን እያልን እንጠራታለን አምባ መጠጊያ መመኪያችን ከክፋ ቀን መከለያችን እናተታችን  እመአቤታችን ታቦት ዘዶር ድንግልን እንደ ቅዱሳኑ ኪዳነምሕረት እመቤትለዓም ሁሉ መድኃኒት እያልን ሰንማጸናት ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍ ነጻ ታወጣናለች እና እስከመጨረሻው ድረስ በሃይማኖት በምግባር ተወስነን እንድንኖር የእግዚአሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን

No comments:

Post a Comment