Tuesday, April 3, 2012

መልክአ ተክለሃይማኖት

                  መልክአ ተክለሃይማኖት
        እንደ ቤተክርስትያናችን ስርአት የማኛውም ጸሎት መክፈቻ እና መዝጊያ አቡነ ዘበሰማያት ነው የግልም ሆነ የማኅበር ጸሎት ሲጸለይ አቡነ ዘበሰማያት ግድ ነው ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ጸሎቶችን እያንዳንዱ ክርስትያን በእለቱ በአል መሰረት ወይም ወዳጅ እንዳደረገው ጻድቅ የመረጠውን ቅዱስ ውዳሴ፤ገድል፤ድርሳን ወይም መልክ ማድረስ ይችላል ። ቅዱስ መጽሃፍ ሌሎች ከአዋልድ መጻህፍት የተውጣጡ ጸሎቶችም ሆነ የግል ጸሎት እንዳይትጸለይ አይከለክልም ጌታችን ለአብነት ለመነሻ ያህል ካሳየን በኋላ ለደቀመዛሙርቱ በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አምልተው አስፍተው ስርአት እንደሚሰሩ አስቀድሞ ነግሮቸዋ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከሚጸለዩ የጸሎት አይነቶች አንዱ መልካ መልክ ነው

                         
          ከዚህ ንባብ እንደምንረዳው ጌታ በልበ ሃዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ቀለምነት የጻፈው ብዙ የቤተክርስትያን ስርአት እንዳለ ነው። ሃዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ከትቃኙ በኋላ አእምሮአቸው ሰፍቶ ቀድሞ መሸከም ያልቻሉት ምስጥር ሁሉ ትገልጦላቸው ለበተክርስትያን ጸሎቱን ስራአቱን አስተካክለው አውርሰውናል በእግረ ሃዋርያት የተተኩ አበው ልጆቻቸውም አረፍተ ዘመን የገታቸውን የአባቶቻቸውን የሃዋርያትን ተግባር ፈጽመዋል ለዚህም ነው ንዋየ ኅሩይ የተባለ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዝሙሩን ጢሞትዮስን ሲመክረው እንዲህ ያለው"አንተ ግን ትምህርቴን አካሄዴን አሳቤንም እምንቴንም ትእግስቴንም ፍቅሬንም ጽናቴንም ስደቴንም መክራዬንም ትከተልህ" 2ጢሞ3፡10 "የምነግራችው ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አለኝ አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይናገርም የሚመጣውንም ይነግራችኋል" ዮሓ 16፡12-13"እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀት እና በቀለም ልጽፈው አልወድም ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍ ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ " 2ዮሃ1፡12በማለት አባቶቻችን ሃዋርያት ለደቀመዛሙርቶቻቸው በጹፍ ብቻ ሳይሆን በቃል ጭምር ብዙ ስርትአቶችን እንዳስተላለፉላቸው አስረድቶናል ከአባቶቻችን በመስማትና በማየት የምንወርሳቸው ስርአቶች ለክርስትና ህይውታችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው ታላቁ ሊቅ የ እስክንድርያው ቅዱስ ቄርሎስ ስለ ትውፊት ሲናገር
             ሐዋርያው ጢሞትዮስን ሲመክረው ቅዱስ ጳውሎስን  በጹሑፍ ብቻ ሳይሆን ብቃልና በተግባር ያሳየውን ሁሉ እንደተከተለው ገልጾለታል ቤተክርስትያን ዛሬ የምትጸልያቸው ጸሎቶች ሁሉ ከአባቶቻችን በቃልና በተግባር ካስተማሩት የተወረሰ እንጂ እንደ እንግዳ ደራሽ እነደወንዝ ፈሳሽ የመጣ አይደለምአባቶቻችን ሃዋርያት ሁሉንም ስርአት በመጽሃፍ ቅዱስ አልጻፉትም እንደውም ከተጻፉት ይልቅ ሳይጻፉ በትውፊት የደረሱ መረጃውች እጅግ ብዙ ናቸው ። ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሃንስ በመልዕክቱ

         "በቃል የደረሱንን እውነተኛአስተምሮውችንንና የአበውን ትውፊት እከተላለው" Quasten: patrology vol 3,p136

እንግዲህ ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደተሞከረው ቤተክርስትያናችን ብጽሁፍ እና በትውፊት ተቀብላ ከምትጸልያቸው የጸሎት አይነቶች አንዱ መልካ መልኮችን የሚያካትት ጸሎት ነው በዚህ ጽሑፍ የአባታችን የቅዱስ ተክለሃማኖትን መልክ የሚመለከተውን ጸሎት እንዳስሳለን አምላከ ተክለሃማኖት ማስተዋሉን ያድለን አሜን

                                መልክ ማለት ምን ማለት ነው? 
          መልክ የአካል ክፍል ሲሆን እንደ የአገባቡ የተለያየ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል ለምስሌ "መልከ መልካም " በሚለው ሃረግ ውስጥ ውበትን ያመለክታል በሌላ አገባብ ደግሞ "መልኩ ጠይም ነው" ሲባል የቆዳ ቀለምን ያመልክታል በዚህ ጸሎት ላይ "መልክአ" ሲባል ደግሞ ሕዋሳትን መላው የአካል ክፍሎችን ያመለክታል ይህም በውስጥ እና በውጭ ያሉትን በሙሉ የሚያካትት ነው ከዚህ በተጨማሪ መልኩ የሚደርስለትን ጻድቅ መልክዐ ንጽህናውን ምግባሩን ትሩፋቱን መንፈሳዊ ተጋድሎውን በስነግጥም መልክ የሚያትት ነው የሚጸልየውም ሰው መልኩ በሚደርስለት ጻድቅ ቃልኪዳን እየተማጸነ በረከት ያገኛል። ይህም ጠቢቡ ሰለሞን

             "የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው " ምሳ10፤7
"ጻድቃን ሆይ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ለቅኖች ምስጋና ይገባል" መዝ32(33)፡1ባለው መሰረት ቅዱሳን የበረከት ምንጭ ስለሆኑ ነው ዋናው ቁም ነገር የቅዱሳንን ሕዋሳት እያነሱ ማወደስ እና መማጸን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ነው ወይ ? የሚለው ነው ። ከሁሉ በፊት መረዳት የሚገባን ለእግዚአብሔር ሰዎች በጸጋ ምስጋና እንደሚገባቸው ነው ለዚህም ነው መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት እንዲህ በማለት የዘመረውእንግዲህ ለቅኖች ምስጋና ከተገባ መላ ሕዋሳቶቻቸው ቢወደሱ ምንድነው ችግሩ? የቅዱሳንን ሕዋሳት መልክ እያነሱ ማወደስ ከጥንት የነበረ መጽሕፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ነው። ይህንንም ለማስረዳት ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል
- "መልካሙን የምስራች የሚያውሩ እግሮቻቸው እን ዴት ያማሩ ናቸው" ኢሳ52፡7
            በዚህ ንባብ ውስጥ መልካሙ የምስራች የተባለ ወንጌል ነው ውንጌል ማለት የምስራች ማለት ነው ስለወንጌል እየተዘዋወሩ የሚያስተምሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው በማለት ነብዩ ከሕዋሳት አንዱ ለሆነው ለእግራቸው ምስጋና በአድናቆት ሲያቅርብ እንመለከታለን ስለዚህ ቅዱሳን መላ ሕዋሳቶቻቸውን የጽድቅ ንዋይ አድርገው ስላቀረቡ ከራስ ጽጉራቸው አንስቶ እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ መልክ ቢደረስላቸው ውዳሴ ቢቀርብላቸው ትክክል ነው የነብያትን ፈለግ መከተል ነው

-" መልኩም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር ፊቱም እንደ መብረቅ ምስያ ነበር አይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና ክንዶቹም እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ ............ "ዳን 10፡6

በማለት በግልጽ የመልአኩን መልክአ ሲያወድስ እንመለከታለን ታድያ መልክአ ሚካኤል ፡መልካ ገብርኤል ... ወዘተ ቢደረስ ምንድነው ስህተቱ? መጽሃፍ ቅደኡሳዊ መሰረት የያዘ አይደለምን?
-"የእናንተ አይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብጹአን ናቸው" ማቴ 13፡16
ይህ ቃል የክብር ሁሉ ባለቤት ራሱ ገታችን የተናገረው ኃይለ ቃል ነው ። ከንባቡ መረዳት እንደሚቻለው ጌታ ጽድቅን ለመስማት የታደሉ ጆሮዎችን ብጹአን እያለ ሲያመስግን እንመለከታለን እንግዲህ ጌታ ራሱ ለመልክአ ቅዱሳን ምስጋና መነሻ የሚሆን አብነት ካሳየን እርሱን ተከትለን የቅዱሳንን መልካ መልክእ ብናደርስ የጌታ ወዳጆች የሚያሰኝ እንጂ አንዳንድ ሰነፎች እንደሚሉት የሚያስወቅስ ምንም ነገር የለም
-        "የተሸከመችህ ማኅጸንና የጠባሃቸው ጡቶች ብጹዓን ናቸው " ሉቃ11፡27
በማለት አንዲት ሴት ለእመቤታችን መልክአ ማርያም በምታደርስበት ጊዜ ጌታችን ውዳሴዋን አልተቃወመም ይልቁንም በቁጥር 28 ላይ ስንመለከት "አዎን" በማለት ምስጋናዋን ሲቀበለው እናያለን በእርግጥ ይህቺ ሴት የጌታችን የባህሪህ አምላክነት የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት ገብቷት ከልቧ ያቀረበችው ምስጋና ቢሆን ምንኛ መልካም ነበረ ነገር ግን እናቱን ባመሰግንለት እኔንም ያመሰግነኛል ብላ ውዳሴ ከንቱን ሽታ በማመስገኗ ምስጋና የሚገባቸው እነማን እንደኦኑ ተነግሮአታል የሆነው ሆኖ ግን ለእመቤታችን የቀረበው ምስጋና ትክክል መሆኑን "አዎን "በማለት ጌታ አረጋግጦአል እንግዲህ ልብ እንበል በቅዱስ መጽሃፍ የእመቤታችን ጡቶቿ ማኅፀኗ ተመሰገኑ ማለት መልክአ ማርያም ተጻፈ ማለት አይደለምን? ይህንን መነሻ አድርገን መላ ሕዋሳቶቿን ብናወድስ በርግጥ ትክክል ነን ማለት ነው።
ለመግብያ ያህል ይህን ካልን ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳያችን እንመለስና እስከ አሁን መልክ ማለት ምን ማለት እንደሆነና መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ጸሎት መሆኑን ከብዙ በጥቂቱ ለማሳየት ሞክረንናል ከዚህ በመቀጠል ደግሞ መልክአ ተክለሃይማኖት ብጸሎትነት ደረጃ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ይዘቱን አንድ በአንድ ለመመልከት እንሞክራለን አምላከ ተክለሃይማኖት ማስተዋሉን ያድለን አሜን ።
                     ሰላም ለፅንሰትከ
                     ፩ "ሰላም ለፅንሰትከ ውለልደትከ እምከርሥ።
                          አመ ዕሥራ ውረቡዑ ለወርኃታኅሣሥ።
                          ተክለሃይማኖት በኩሉ ወበውስተ ኰሉውዱስ ።
                           ናሁ ወጠንኩ ወዕቤ ለስብሓቲከ ሓዲስ ።
                            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።"
ትርጉም .፧ "ተክለ ሃይማኖት ሆይ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀንስከው ፅንሰትህና በታህሣሥ ሃያ አራት ቀን ለተወለድከው መወለድም ሰላም እላለው።ይህ ክፍል የአባታችንን
                    1.ፅንሰታቸውን
             
2.ልደታቸውን የሚያወድስ ሰላምታ የሚሰጥ ንባብ ነው 
                    በቅዱስ መጽሃፍ የቅዱሳን ፅንሰታቸው ልደታቸው በተለየ ሁኔታ ሲወደስ ሲከበር በብዙ ስፍራ ተጽፎ እናገኛለን የአባታችን የቅዱስ ተክለሃማኖት ፅንሰታቸውም ልደታቸውም በፈቃደ አምላክ በብስራተ መልአክ ነው ። ቅዱሳንን እግዚአብሔር አምላክ በማህፀን እንደሚመርጥ የተረጋገጠ ነው ነብዩ ኤርምያስን
" በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለው ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሼሃለው ለአሕዛብም ነብይ አድርጌሃለሁ" ኤር፩፤፬-፭
በማለት አምላክ አንዳንድ ወዳጆቹን መምረጥ የሚጀምረው ከማህፀን መሆኑን በግልጽ አስቀምጦልናል በዚህም መሰረት
አባታችን የቅዱስ ተክለሃማኖትም ከፅንሰት ጀምሮ የተቀደሱ የተመረጡ መሆናቸውን ገድላቸው ይናገራል
"የተመረጠ ልጅ ዛሬ በማኅፀንሽ ትፀነሰ በእግዚአብሔርና በእመቤታችን ዘንድ የተወደደ
በመላእክትም ዘንድ እጅግ ይከበረ ነው" ገድለ ተ/ክ15፡7
                 የቅዱሳን ልደታቸውም እጅግ የከበረ ነው የፅንሰታቸው የልደታቸው በረከት በቃልኪዳናቸው ለሚታመን ሁሉ የሓሴት የደስታ ምንጭ ነው የመጥምቁ ዮሓንስ ልደት በተበሰረበት ክፍል እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል
"ደስታና ተድላ ይሆንልሃል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል"ሉቃ 1፡14-15
ስለዚህ የቅድሳኑ ፅንሰታቸው ልደታቸው ለኛ ተድላችን ደስታችን ነው ። በፅንሰታቸውና በልደታቸው ቅር የሚለው ካለ እርሱ በቅዱሳኑ ገድል ትሩፋት ያፈረ የዲያቢሎስ ወገን ብቻ ነው ምክንያቱም ቅዱሳኑን የሚዋጋ ሰይጣን ነውና
            " ማደርያውንም በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ" ራእ 13፡6
አማናዊት ማደርያው ከሆነችው ከእናቱ ጀምሮ በሰማይ ያሉ መላእክትን በአጸደ ነፍስ ያሉትን ቅዱሳንን ሁሉ የሚሳደብ የሚዋጋ አውሬው ዲአብሎስ ነው ። ሴይጣን በሰዎችም ሲያድር ለቅዱሳኑ የሚገባውን ክብር እንዳይሰጡ ነገረ ቅዱሳንን መስማት እንዲጠሉ ያደርጋል አልፎ ተረፎም አንደበታቸውን አንደበቱ አድርጎ ይጸርፋል ይሳደባል።እውነተኛ ክርስትያኖች ግን ቅዱሳኑ የተወለዱበትን የተፀነሱበትን ቀን እያሰቡ ተድላ ድስታ በአል ደርጋሉ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ተብሎ እንደተጻፈ የቅዱሳኑን ፅንሰትና ልደት በማሰባችን በማክበራችን የምናገኘው ጥቅም ብዙ ነው

  • 1.በረከት እናገኛለን "የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ10፡7
  • 2.በቃል ኪዳናቸው እንጠቀማለን "ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርግሁ" መዝ 88፡3
  • 3.ከሕይወታቸው እንማራለን "የኑሮአችውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው" ዕብ 13፡7
  • 4.የእግዚአብሄርን ጸጋ እናደንቃለን "እግዚአብሄር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67፡35
ጥቂቶቹ ናቸው ታድያ ቅዱሳኑን ማሰብ በአላቸውን ማክበር ይሄን ያህል በረከት ካለው ሃዋርያው እንዳለው ጊዜ አይበቃንም እንጂ ቢቻለን አረፍተ ዘመን እስኪገታን ለትውልዱ ስለቅዱሳኑ ብናወራ ምንኛ መልካም በሆነልን
".........ስለዳዊት ስለሳሙኤልም ስለነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና" ዕብ11፤32

No comments:

Post a Comment