የቤተክርስቲያን የቀን መቁጠሪያን ያዘጋጀ ድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ ነው!ድሜጥሮስ ማለት መስተዋት ማለት ነው፡፡ ሀገሩ እስክንድርያ ነው፡፡ አባት እናቱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋጎች ነበሩ፡፡ ላባቱ ወንድም ሴት ልጅ ነበረችው ሲሞት ልጄን ከልጅህ አትለይብኝ ብሎት አብሮ አሳድጓቸዋል፡፡አካለ መጠን ሲያደርሱ ዘመኑ አረማውያን የበዙበት አማንያን ያነሱበት ነበርና ከሌላ ብናጋባቸው ከሃይማኖት ከገቢረ ሠናይ ይርቃሉ፤ ሕገ ነፍስ ከሚፈርስ ሕገ ሥጋ ይፍረስ ብለው አጋቧቸው፡፡ በልተው ከጠገቡ ጠጥተው ከረኩ በኋላ ሥርዓተ መርዓዊ ወመርዓት ያድርሱ ብለው መጋረጃ ጣሉባቸው፡፡ እሷ አስቀድማ ድሜጥሮስ ያንተ ወንድምነት ለኔ የእኔ እኅትነት ላንተ አልበቃ ብሎ የባዕድ ሥራ እንሥራ አለችው፡፡ እኔስ የአባት የእናቴን ፈቃድ ልፈጽም ብዬ እንጂ ፈቃዴ አይደለም፤ በዚያውስ ላይ አንቺ ከፈቀድሽ ብንተወው እንችል የለምን? አላት እንተወው አለችው፡፡ እንኪያስ አንቺንም ለሌላ እኔንም ለሌላ እንዳያጋቡን መስለን እንኑር አላት፡፡ በዚህ ተስማምተው አንድ ምንጣፍ እያነጠፉ አንድ ዐጽፍ እየተገናጸፉ 48 ዘመን ኖሩ ፡፡ ምነው “መኑ ይክል ሐቁረ. እሳት በሕጽኑ ይል የለምን እንደምን ይቻላል? ቢሉ ሕሩይ ለንጽሕና ነውና አንድም እሳቱን እንዲታፈኑ ማድረግ ለጌታ ይሳነዋልን? መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቀኝ ክንፉን ለርሱ ግራ ክንፉን ለርሷ አልብሶ አድሮ ሲነጋ በአምሳለ ርግብ በመስኮት ወጥቶ ሲሄድ ያዩት ነበር፡፡
Thursday, September 10, 2015
Saturday, January 17, 2015
ጥምቀተ ክርስቶስ
ጥምቀተ ክርስቶስ
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን
በኢትዮዽያ አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርዓት መሰረት በየዓመቱ ጥር 11 ቀን በታላቅ ድምቀት የጥምቀት በዓል ይከበራል ለመሆኑ ጥምቀት ምን ማለት ነው ? እና በሌሎች በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን
ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መላ ሰውነትን በተቀደሰ ውኃ መነከር ወይም መዘፈቅ ውሰጥ ገብቶ መውጣት መነከር መውጣት መቀበር ማለት ነው አንድ ሰው በመጠመቁ ክርስቶስን በሞቱ ይመስለዋል ይኸውም ተጠማቂው ከቅዱሱ ውኃ ሲነከር በክርስቶስ ሞቶ ሲመስለው ከውኃ ሲወጣ ደግሞ ክርስቶስን በትንሣኤው ይመስለዋል፤ በዚህም ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናል፡Tuesday, January 6, 2015
ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ
ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ
“ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዓቢየ ወለአለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ”
ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ
በድንቁርናና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ፍጹም እውቀት ተሰጣቸው፤ ሞት ባመጣው ምስል ሞትን በመምሰል ለነበሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍስ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው፤ በኃጢአት ለነበሩ ስርየት፤ በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተሰጣቸው ኢሳ.ም 9፣2እግዚአብሔር የሁላችን አባት አዳምን በአርአያውና በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ባረከው ሁሉንም እንዲገዛ እንዲነዳ ሥልጣን ሰጠው፤ በረከቱን፣ ሥልጣኑንና ሲሳዩን ከሰጠው በኋላ ፈጣሪውን የሚያስታውስበት ትዕዛዝ አዘዘው፡፡ ትዕዛዙም የፈጣሪና የፍጡር መለያ፣ የአዛዥና የታዛዥ ገደብ፣ ሰው ለሕግ መገዛት እንደሚገባው ለማስረዳት የተደረገ እንጂ የስስት ወይም የንፍገት አልነበረም፡፡
ይህንን ደግሞ አዳምም ሆነ ሔዋን ያውቁታል፤ በምግብ እጦት እንዳይቸገሩ ግን በገነት ያሉትን አትክልት እንዲበሉ ከውኃውም እንዲጠጡ ፈቅዶላቸዋል፡፡ሰው ግን ከፍጥረት አክብሮ አልቆ ያነገሠውን እግዚአብሔርን አስቀይሞ በተሳሳተ ምክር ተመርቶ አትብላ የተባለውን ዕፀበለስን ስለበላ ከፈጣሪውም ትዕዛዝ ስለወጣ በዚህ ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)