Monday, May 21, 2012

«ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም» ለምን ተባለ ?


       «ያለመቃብሩየመዳንተስፋየላችሁም»ለምንተባለ?"ክፍ3                                       
               <<ወአልብክሙ ተስፋ ድኂን ዘእንበለ መቃብሪሁ»                            
        በክፍል ሁለት ጽሑፋችን ሊቀ ጳጳሱ <<ወይ ሰው የነፍሱን ድኅነት ሳያውቅ ይጎዳል >>የሚለውን አባባል ምን ማለት እንደሆነ ተመልክተን ነበር ያቆየነው በዚህ ጽሑፋን ደግሞ  ቀጣዩን ክፍል ይዘንላችሁ ቀርበናል የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን ያድለን አሜን

      አስቀድመን  እንደተመለከትነው ሊቀ ጳጳሱ ሰው የነፍሱን   ድኅነት  ሳያውቅ ይጎዳል ብሎ አላቆመም ተገቢውን ምክር እንዲህ በማለትቀጠለ «መድኃኒታችሁንተዋችሁትሕይወታችሁንምጠላችሁትጌታ ለተክለሃይማኖት በአፅምህ ቦታ የተቀበረውን  ዘወትርም ከእሷ ዘንድ የሚኖር በኋላኛይቱ ቀን በግልጽ ካንተ ጋራ ይለፍያለውን አልሰማችሁምን አላቸው»በእውነትም የቅዱስ ተክለሃይማኖት የቃልኪዳኑ በረከት መድኃኒት ነው ሕይወት ነው ጳጳሱም ሊመሰክር የፈለገው ይህንኑ ነው።አንዳንዶች ግን በሰነፍ አእምሮአቸውሲሳሳቱ እየተመለከትን ነው ሰይጣን ሰዎች በቅዱሳኑ በረከት እንዲጠቀሙ ስለማይፈልግ የማይጋጨውን ያጋጭባቸል ለምሳሌ የቅዱሳኑን ክብር  የሚቃወም የተሐድሶ ብሎግ ስለዚህ ቃል የተሳሳተ ማብራርያ ሲሰጥ እንዲህ ብሎ ነበር የጻፈ   
 « በጣም የሚያስቀው ግን የጳጳሱ መልስ ነው። «ወይ ሰው የነፍሱን ድኅነት ሳያውቅ ይጎዳል መድኃኒታችሁን ተዋችሁት ሕይወታችሁንም ጠላችሁት» አለ ሊቀ ጳጳሱ። መድኃኒታችሁ እና ሕይወታችሁ ሲል የተክለ ሃይማኖትን መቃብር ሰብኳል። እንደዚህ ዓይነት ስብከት የሚሰብክ ጳጳስ በክርስቶስ አምኖ ተምሮ ለሊቀ ጵጵስና የደረሰ? ወይስ ትንሽ ጠጅ ቀምሶ ሞቅ ያለው ደብተራ ይሆን? እንጃ ላንባቢ ብተወው ይሻላል። ጎበዝ! ከመቃብር ምን ዓይነት መድኃኒት ይገኛል? በመቃብርስ ምን ሕይወት አለ? ሕይወትና መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በኢትዮጵያ ካሉት የቅዱሳን መቃብር ሁሉ የተክለ ሃይማኖት መቃብር ሕይወትና መድኃኒት የሆነበት ምክንያት የደብረ ሊባኖስ ፖለቲካ አይሎ በመገኘቱ ነው እንጅ ሌላ አይመስለኝም።»
           እግዚአብሔርያሳያችሁ የእግዚአብሔርን ቃል አይመስለኝም ይመስለኛል ብሎ ማስተማር ምን ማለት ነው ? ትምህርቱ ራሱ ከስጋና ከደም የተገኘ ግለሰባዊ አስተያየት ለመሆኑ ግልጽ ነው  ። በመሰረቱ በቅዱሳኑ ላይ እግዚአብሔር የሚሰራው ድንቅ ስራ ከጌታ ማዳን ጋር በምንም መልኩ አይጋጭም  ቅዱሳን ማለት የክርስቶስ ማዳን የሚገለጽባቸው ምርጥ እቃዎቹ ናቸው                                                                                         «እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው» መዝ ፷፯፡፴፭                          
 « እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ»  መዝ ፬፡፫                                           
                 ከጌታ ድንቅ ስራዎች አንዱ ዋናው የሰው ልጆች መዳን ነው ቅዱስ              መጽሐፍ እንደሚያስተምረን ጌታ ድንቅ ስራውን በቅዱሳኑ እንደሚገለጥ ነው  ታድያ              የጌታ ድንቅ  ማዳን በቅዱሳኑ ተገለጠ ቢባል ምን የሚያስተች ነገር አለ ? ይህ ማለት                ቅዱሳን ስጋቸውን ቆርሰው ደማቸውን አፍሰው እንደ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅለው              አዳኑን ማለት አይደለም ነገር ግን በጌታ ያገኘነውን ማዳን እንድንጠቀምበት ምክንያት ይሆኑናል ማለት ነው ። ጌታ በቅዱሳኑ በሁለንተናቸው ያድናል በልብሳቸው ያድናል ፤ በጥላቸው ያድናል፤ በመቃብራቸውም ያድናል ይህንንም በክፍል ሁለት ጽሁፋን ስለተገለጸ መመልከት ይቻላል ። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ እንዲድኑ ነው  የሰው ልጅ ደግሞ ስጋ ለባሽ ስለሆነ ሁሌ ይበድላል መዳናችንን የሚፈልግ እግዚአብሔር ደግሞ ሌላው ቢቀር በቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ስርየተ ኃጢአት አግኝተን እንድን ዘንድ ፈቃዱ ሆነ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከምንም በላይ የሚገለጸው በቅዱሳኑ ላይ ነው  ማዳኑም የሚገለጸው በቅዱሳኑ ነው ይህን በተመለከተ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እንዲህ ይላል                                                             
« ፈቃድህ ሁሉ በምድር ላይ ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው» መዝ፲፭፤፫ እንግዲህ ፈቃዱ ሁሉ  በቅዱሳኑ ላይ ከሆነ  ማዳኑን በቅዱሳኑ አይገልጽም ማለት ይቻላልን ? አይቻልም ስለዚህም ከላይ በተመለከትነው ታሪክ ሊቀ ጳጳሱ የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ቃልኪዳን አስታውሶ መድኃኒታችሁን ቢል በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው  መቼም ማንም መጽሐፍ ቅዱስን አምናለው የሚል ሁሉ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ መቃብር ሳይቀር ስዎችን እንደሚያድን ሊጠራጠር አይችልም  በኤልሳ መቃብር ሙት ያዳነ አምላክ ዛሬም ኃይሉ አይደክምም ማዳኑም አይከለከልም እንደ ኤልሳ ባሉ ቅድሳን በነ ቅዱስ ተክለሃይማኖት መቃብርም ያድናል[፪ነገሥ ፲፫፡፳፩] ይህም ለወዳጆቹ ያለውን ፍቅር የሚያስረዳበት ሌሎችም የቅዱሳንን ፈለግ ተከትለው ገድል ትሩፋት ቢፈጽሙ ለሌሎች የሚተርፉበት ይህን ያህል ጸጋ እንሚሰጥ የሚያስረዳበት ነው ።እንኳንስ በመቃብራቸው ቀርቶለጊዜው በፀሐይ ግርዶሽ በሚፈጠረው ጥላቸው እንኳን እግዚአብሔር የማዳን ስራውን ሲሰራ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎአል[የሐዋር፭፤፲፭] 
                እንግዲህ ምን እንላለን ተሐድሶዎቹ በብሎጋቸው እንዳሉት ልዑል እግዚአብሔር በቅድሳኑ በሚሰራው ድንቅ ስራ ማመስገንን ትተን እንሳቅን ? ይህስ ለክርስትያን የማይገባ ተግባር ነው። ደግሞስ በመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳኑ መቃብራቸው ፤ ጥላቸው እና በለበሱት ጨርቅ ሳይቀር ይፈውሱ እንደነበር የተጻፈው ተሐድሶዎቹ እንደሚሉት በወይን ስካር ይሆንን ?እንዲህስ ማለትን እግዚአብሔር ከኛ ያርቅልን  ለእነሱም ማስተዋሉን ያድልልን ። እኛስ በተረዳንበት እውነት እንጸናለን ጸጋውን ያለንፍገት አብዝቶ በቅዱሳኑ ላይ በሚገልጽ ልዑል እግዚአብሔር እንታመናለን  ። ይቆየን     


2 comments:

  1. bewnet ejachhun yaberta!!!!!!!!!!!!
    we search such type of blogger for a long time ..........thanku !!!!!!!!!!

    ReplyDelete