የሕማማት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
1 በሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም አናማትብም ? የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀለ ከተሰቀለ በኋላ ነው በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልገሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ሕማማት በቤተክርስተያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ የማማተብ ስርዓት የለም
2 በሰሞነ ሕማማት ለምን አንንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቶአል እኛም እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችችንን ለማሰረዳት ከዚሀ በተጨማሪም ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰሞነ ሕማማት እሰከ ምሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም
3 በሰሞነ ሕማማት የማይፈቀዱ ሌሎቸ ነገሮች ምን ምን ናቸው ? ማንኛውም ለስጋ የሚያደሉ ተግባሮችን መቀነስ እና ቢቻለን አበዛኛውን ጊዜአችንን በቤተ እግዚአብሔር የጌታን መከራ ሕማም በማሰብ በፆም በስግደት በጸሎት ማሳለፍ

በትዳር ያሉ በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ
ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ
4 ስለ ሰሞነ ሕማማት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ አለን?
ነብዩ ኢሳይያስ "በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሞአል " ኢሳ53፤4 ይላል ሕማማት የሚለው ቃለ በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወሰደ ሲሆን የጌታን መከራ የምናስብበት ሳምንት ነው የጌታችንን ሞቱን ሕማሙን ማሰብ መዘከር እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ እነዲህ ይላል

" ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና" 1ቆሮ11፤26
ይህ ሳምንት ለአይሁድና ለመሰሎቻቸው የደስታ ወቅት ቢሆንም ለክረስትያኖች በጥልቅ ኅዘን ውስጥ የሚገቡበት ሳምንት ነው እንዲሀ ተብሎ እንደተጻፈ'' እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ ዓለም ግን ደስ ይለዋል እናንተም ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል'' ዮሐ16፤20
በእርግጥ ኃዘናችን ትንሳኤውን እሰክናይ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም ግን እናዝናለን በትነሳኤው ደግሞ ደስታውን እንካፈላለን።
ሰኞ አይሁድ እንዴት እንደሚይዙት ለመማከር ክፉ ጉባኤያቸውን ጀመሩ
''በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ ጌታ ኢየሱስንም በተንኮል ሊያስይዙት ሊገሉትም ተማከሩ" ማቴ26፡3_4
ይህንን ጉባዔ ቅዱሰ ዳዊት የከፉዎቸ ጉባዔ እያለ ይጠራዋል
"ብዙ ውሾች ከበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ" መዝ21፤16
አይሁድ ሰኞ የጀመሩትን ዕረቡ ውሳኔአቸውን አጠናቀው በምሴተ ሐሙስ ከዕራትና ከቁርባን በኋላ ሰይፍና ጎመድ ይዘው መጡ በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ሰጣቸው ያዙትም እስከ አርብ ስድስት ሰአት ሲያንገላቱት ቆይተው ከበዙ መከራ በኋላ ሰቀሉት ዘጠኝ ሰአት ላይ ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ከቅዱስ ስጋው ለየ ከአሰራ አንድ ሰአት በፊት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በምስጋና ገንዘው ቀበሩት ።
ከሕማሙ ከመከራው በረከት ያሳትፈን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

No comments:
Post a Comment