Friday, April 6, 2012

«ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም» ለምን ተባለ ?

           "ወአልብክሙ ተስፋ ድኂን ዘእንበለ መቃብሪሁ»                              «ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም»      ክፍል አንድ 
"ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር እንድወስድ እሺ ትለኝ ዘንድ እለምንሃለው     እግዚአብሔርም  ለኔ ለባሪህ በዚህ  ነገር ብቻ ይቅር ይለበለኝ" ፪ነገሥ፭፤፲፯

         ይህ ቃል  መኮንኑ ንዕማን ውደነብዩ ኤልሳዕ ሄዶ ታአምራት ከተደርገለትበኋላ ያቀረበው ጥያቄ ነበር። ነብዩ ኤልሣዕም ሃሳቡን ተቀብሎ በደኅና ሂድ ብሎ አስናብቶታል ። 
      ንዕማን በአገሩ እግዚአብሔር አይመለክም ስለዚህም ለአምልኮተ እግዚአብሔር ይረዳው ዘንድ የእግዚአብሔር ሰው ኤልሣዕ ካለበት ስፍራ አፈር ጭኖ ይዞ ሄደ በዚህም ይቅርታ ምህረት እንደሚያገኝ አመነይህ ማለት ዳነ ማለት አይደለምን? መዳን ማለት እኮ መደ አምልኮተ እግዚአብሔር መመለስ ለእግዚአብሔር እየተገዙ መኖር ማለት ነው ።
ከዚህ በተጨማሪም የቅዱሳኑ አጽም ያረፈበት መሬት ሙታንን እንደሚያስነሳ  በቅዱስ መጽሓፍ እንዲህ ተብሎ  ተጽፎአል  
 "ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ ሬሳውንም በኤልሣዕ መቃብር ጣሉት የኤልሣዕን አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዬው ድኖ በእግሩ ቆመ"   ፪ነገ፲፫፤  
         እንግዲህ ምን እንላለን? ቅዱሳን ገድል ትሩፋት የፈጸሙበት የተቀደሰ አጽማቸው ያረፈበት ስፍራ ስፍራ አያድንም እንላለን? በፍጹም ይልቁንም ላመኑበት በስጋም በነፍስም ደኅንነት ያስጣል እንጂ።ይህንለማለትያነሳሳን በአባታችን በቅዱስ ተክለሃይማኖት ገድል ላይ  ገድ/ ተክ/ ሃይማኖት ም  ፶፰ቁ ፲
      ግእዙ   "ወአልብክሙ ተስፋ ድኂን ዘእንበለ መቃብሪሁ» 
         አማርኛው  «ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም»    
  የሚለውን ከሙሉ ታሪኩ ተቆንጽላ የተወሰደች ንባብ ይዘው ገደለ ተክለሃይማኖትን ለማብጠልጠል የሚፈልጉ የስህተት መልክተኞች ስላሉ መእመኑ ብቂ ግንዛቤ እንዲወስድ ከማሰብ ነው በመሰረቱ ከላይ በመጠኑ ለማብራራት እንደሞከርነው ቅዱሳን ገድል ትሩፋት በፈጸሙበት የተቀደሰ አጽማቸው ባረፈበት ስፍራ ከሌሎች ቦታዎች ይልቅ የእግዚአብሔር ማዳን እንደሚገለጽበት ተመልክተናል   ። በአባታችን በቅዱስ ተክለሃይማኖት ገድል ላይ ይህ ቃል ለምን እንደተባለ ሙሉ መዕራፉን በመመልከት እግረ መንገዳችንን ለህይወታችንም እጅግ ጠቃሚ ምክር እናገኝበታለን                                                                               ታሪኩ እንዲህ ነው ሁለት መነኮሳት ከደብረሊባኖስ ተነስተውበረከት ለማግኘት ወደ ኢይርሩሳሌም ጉዞ  ይጀምራሉ ከስክንድርያውሊቀጳጳስዘንድደርሰውከተባረኩበኋላከወዴትናችሁአላቸውከኢትዮጵያከቅዱስተክለሃይማኖትአጽሙካረፈበት ከመቃብሩ ስፍራ እንደመጡነገሩትሊቀጳጳሱም ከተቀደሰ የቃልኪዳን ስፍራ እንደመጡ በተረዳጊዜ ከመሬት ወድቆ ሰገደላቸው የእግራቸውንም ትቢያ ሳመ      
          ሊቀጳጳሱ ይህን  ማድረጉ ሶስት ነገር ያስተምረናል  
                           ፩ እንግዳ ተቀባይነትን                   
                            ፪ ትህትንናን               
                         ፫  የቅዱሳንን በረከት ይህ ስርአት እንደ እንግዳ ደራሽ የመጣ ሳይሆን  ከጥንት በመጽሃፍ ቅዱስ የነበረ ትውፊት ነው እንግዳ ሲመጣ እጅ ነስቶ መቀበል በተለይ  ሰዎች ከተቀደሱ ገዳማት ሲመጡ እግር ስሞ በረከት መቀበል የተለመደ ጥሩ ሊበረታታየሚገባው ክርስትያናዊ ትውፊት ነውበእንግዳ ተቀባይነት በትህትና  ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች እግር በመሳም  በመስገድ አክብሮታችውን ሲገልጹ በመጽሃፍ ቅዱስ ተጽፎ እንያለን ከነዚህም ለአብነት ያህል የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል
ታላቁ የሃይማኖት አባት አብርሃም ብትህትና እና በአክብሮትለኬጢልጆች እና ለምድሩ ህዝብ    ሰግዷል ዘፍ፳፫፤፯ 
ያዕቆብና ቤተሰቦቹ በአክብሮትና በትህትና ለኤሳው ሰግደዋል ዘፍ ፴፫፤፫-፰ 
 የዮሴፍ ወንድሞች ልዮሴፍ በትህትና እና በአክብሮት ሰግደዋል ዘፍ፶፤፲፰
             እንግዲህ ለአክብሮት ለትህትና አንዳችን ለአንዳችን ዝቅ ማለት በመጽሃፍ ቅዱስ የተደገፈ ስርአት ከሆነ ሊቀ ጳጳሱ ከተቀደሰ ስፍራ ለመጡ መነኮሳት ስለ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ክብር ብሎ በትህትና እና በአክብሮት እግራቸውን ቢስም ምን የሚያስተች ነገር አለ እንዲሁም ትህትናው ለሌሎችም በአርያነት ይጠቀሳል እንጂ።ርዕሰ አበው አብርሃም ለኬጢ ልጆች ስለሰገደ ተሳሳተን? አልተሳሳተም ትህትናን እና ሰው አክባሪነትን አስተማረን እንጂ።
      ወደ ታሪኩ እንመልስና ሊቀ ጳጳሱ እግራቸውን ከሳመ በኋላ  ለምን እንደመጡ ጠየቃቸው እነርሱም የነፍሳችንን ደኅነት ልንሻ ብለው መለሱለትበርእግጥም መነኮሳቱ የተቀደሱ መካናትን በመሳለም በረከት በመቀበል ለነፍስ ድኅነት ከሚያሰጡ ተግባረ ነፍስ ከሚባሉ የስነምግባር ክፍሎች አንዱን እየፈጸሙ መሆናቸውን ነበር የገለጹት ይህም ደግሞ እውነት ነው ወደ ተቀደሱ ገዳማት መሄድ በረከት መቀበል ለመንፈሳዊ ህይወታችን ማደግ ከፍተኛ አሥተዋጾ እንዳለው ምንም አያክራክርም  ይህም  ነፍስን የሚያድን ተግባር በመሆኑ ከነፍስ ድኅነት ጋር ቢያያዝ ምንም ሊደንቅ አይገባም ሊቀ ጳጳሱም መልሶ
ወይ ሰው ይነፍሱን ድኅነት ሳያውቅ ይጎዳል  በማለት ጮኽ    ለምን? 
                                                   ይቆየን ይቀጥላል 
                                                ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን

1 comment:

  1. amen---kale hiwot yasemalgn.......... Betam des yemil new........yih tyake bzu gze lerase steyikew neber....... Ahun gin melsun agegnehu.......egziabher yimesgen

    ReplyDelete