፩ሆሣዕናማለትምንማለትነው?
መልስ ሆሣዕና ማለት መዳኃኒት ማለት ነው
፪ ጌታ በአህያ እና በውርንጫ በአንዴ እንዴት ሊቀመጥ ቻለ?
መልስ በሁለቱም በአንድ ጊዜ በታአምራት ተቀምጦባቸዋል ይህም ምሳሌ ነው አህያ የቤተ እስራኤል ውርንጫ የአህዛብ ምሳሌ ሲሆኑ ጌታችን በሁለቱም የሰው ዘር ሊያድር እንደመጣ ያስረዳል
፫ በሆሣዕና ለምን ዘንባባ ይደረጋል?
መልስ በወቅቱ ጌታ በአህያ እና በውርንጫ ተቀምጦ ወደኢየሩሳሌም ሲገባ ህጻን አዛውንቱ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው አመስግነውታል ያንን ለማስታወስ ሲሆን ምሳሌነቱም ዘንባባ ጫፉ እሾኻም ነው እሳት አይበላውም ጌታ ባህሪው የማይመርመር ኃያል መሆኑን ያስረዳናል
፬ ጌታ አህያና ውርንጫይቱን ፈታችሁ አምጡልኝ ለምን አለ

መታሰራቸውን የሚያውቅ ጌታ ፈታችሁ - አምጡልኝ አለ ማንም ቢጠይቃችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ አላቸው ይህም ምሳሌ ነው አህያ እና ውርንጫዋ የአዳምና የልጆቹ ምሳሌ ሲሆኑ መሰረቃቸው የሰው ሊጆች በኃጢአት ምክንያት ዲያቢሎስ ሰርቆአቸው ስለነበር ነው መፈታታቸው በጌታችን የሰው ልጆች ሁሉ ከበደል ከእዳ እስራት ነፃ መውጣታቸውን ያስረዳናል
ተጨማሪ ከሆሣዕና ሊያስተውሏችው የሚገቡ ነጥቦች እነሆ በሆሣዕና ጡት የሚጠቡ ሕጻናት ምስጋናን አቅርበዋል ዛሬም ሕጻናት ከ፵እና ፹ ቀናቸው ጀምሮ የሆሣእናውን ጌታ እንዲያመሰግኑ ከማኅበረ ክርስትያኑ ጋር ይቀላ
"ከሕጻናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ"መዝ፰፤፪-
በሆሣዕና ጌታ በተናቀች አህያ ተቀምጦ አክብሮአታል ዛሬም በትህትና በንስሃ ብንቀርብ ጌታ ያድርብናል ያከብረናል
"ለጌታ ያስፈልጉታል" ማቴ፳፩፤፫ ነውና የተባለው ሁላችንም ለጌታ እናስፈልገዋለን የሁላችንንም መዳን ጌታ ይፈልጋል በሰው ዘንድ ታናናሽ የተባሉት ሳይቀሩ ለጌታ የማያስፈልግ የለም ስለዚህም ስለሁሉ እንጸልይ ሁሉ ተፈተው ወደ ጌታ እንዲመጡ የተቻለንን አስተዋጽዎ ማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችን ነው
ከሆሣዕና በረከት ሁላችንንም ያሳትፈን
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን
It's a good article, keep it up.
ReplyDelete