Thursday, April 19, 2012

ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን?

ክፍል 3ካለፈው  የቀጠለ ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን? 
    ባለፈው የክፍል 1 እና ክፍል 2 ዝግጅታችን ማስነበባችን ይታወሳል በገባነው ቃል መሰረት ቀጣዩን ይዘን  ቀርበናል መልካም ንባብ      
3.እመቤታ ድንግል ማርያም የውርስ   ኃጢአት አለባት ማለት  የጌታችንን ንጹሐ  ባህሪውን መዳፈር ነው   
ጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ስጋና ነፍስን ከሰማይይዞ አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባህሪይ ተዋሕዶ ነውይህን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል"እንግዲህ ልጆቹ በስጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይስለጣንያለውንእንዲሽር-እንዲሁ ተካፈለ የአብርሃምን ዘር  ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም''ዕብ2፤14-15

Sunday, April 15, 2012

ትንሳኤ ክርስቶስ

በኩረ ትንሳኤ  ክርስቶስ

       ርስቶስ ተንሥአ እሙታን                   በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን                     አሠሮ ለሰይጣን                            አግአዞ ለአዳም                                    ሰላም                                     እምይእዜሰ                                        ኮነ                                   ፍስሐ ወሰላ

                                  የዕለቱ ምስባክ

 ወተንሥአ እግዚአብሔር             እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ            ከመዘንቃህ እምንዋም          እንደሚነቃ ተነሣ              ኃያል ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን    የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኀያል            ወቀተለ ፀሮ በድኀሬሁ                 ሰውጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፡፡

  ትርጉም፦
እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ
የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኀያል  
 ሰውጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፡፡
          ትንሳኤ  ክርስቶስ

Thursday, April 12, 2012

ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘዕለተ ዓርብ

                    ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘዕለተ ዓርብ
                                    

  ዐርብ ዘነግህ (1 ሰዓት)
  ቅድመ ወንጌል ተንሥኡ ላዕሌየ
 ሠማዕተ ዐመፃ፣ወዘኢየአምር
       ነበቡ ላዕሌየ፣ ተንሥኡ ላዕሌየ ሠማዕተ ዐመፃመዝ.3411-12)
  ዘማቴዎስ፡- ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይሰቅልዎ ለኢየሱስ  በቀራንዮ መካን፡፡ (ማቴ.261-14)
ዘማርቆስ፡ ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አወጽእዎ አፍአ  ለኢየሱስውስተዐውደምኵናን፡፡ (ማር.151-5)
ዘሉቃስ፡-ወጸቢሖተማከሩ ሊቃነ ካህናት ሐመይዎ ለኢየሱስ
  ወመጠውዎለጲላጦስ፡፡ (ሉቃ.2266-71 231-12)
ዘዮሐንስ፡-   ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ
                   ለኢየሱስ ወነበረ ዓውደ ሶቤሃ፡፡ (ዮሐ.1828-30

Wednesday, April 11, 2012

ሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት

   
ሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት
                       
                                     ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ረቡዕ 
                                     
                       የጸሎተ ሐሙስና በዕለተ ዓርብ ሥርዓተ ጸሎት
                                  
               ሥርዓተ ጸሎተ ዘሰሙነ ሕማማት (ከሰኞ እስከ ሐሙስ)
  
     ትእዛዝ፡ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም

           በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ
                    እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ፡፡
                ‹ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ 
                 ለዓለመ ዓለምአማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል 
                    ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
                        ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ
 
            ‹ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
             ‹ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ 
                እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብልበአኰቴት› ይበሉ
ትእዛዝ፡ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ  አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ።
    ይህንየላይኛውን ጸሎትእያመላለሱ ከአቡነዘበሰማያትጋር 1 ጊዜይበሉ

ሰሙነ ሕማማት ዘሐሙስ

                                                 ሰሙነ ሕማማት  ዘሐሙስ
     ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያው ሐሙስ በቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ 
                            ሀ. ጸሎተ ሐሙስ ይባላል 

             የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን ይማልድ የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ (ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17)
                             ለ. ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል 
አጽበተ  እግር
             ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፤ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብሕን ኃጢአት እጠብ ሲሉ ከአገልጋዮቹ ጀምረው በቤተክርስቲያን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡
                              ሐ. የምሥጢር ቀን ይባላል 

           ከሰባቱ ምሥጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፤ ይኸውም ‹‹ይህ ስለእናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ›› ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ‹‹ይህ ስለእናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ›› በማት እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፤ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል ሆኖ የሚያገለግለውም ጸናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምጻቸውን ዝግ አድርገው፣ በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፤ በቅዳሴውም ጸሎተ ተአምኖ፣ ኑዛዜ አይደረግም፤ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፤ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል-ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡
                      መ. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
ጸሎተ ሐሙስ ( የፋሲካ እራት)          ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ይህ ጽዋዕ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ›› በማለቱ ይታወቃል፡፡ (ሉቃ.22፤20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊ ቃል-ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል-ኪዳኑ ፍጻሜዎች፣ ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡
                        ሠ. የነጻነት ሐሙስ ይባላል
           ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱ ጌታችን ስለሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፡፡›› በማለቱ (ዮሐ.15፤15) ከባርነት የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ በግልጥ ያስረዳናል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት ተላቅቆ፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጐናልና፡፡
በዚህ ዕለት በወንጌላት የተመዘገቡ ድርጊቶችን ቀጥለን እንመልከት
                       ሀ. የፋሲካ ዝግጅት የተደረገበት ዕለት ነው 
        ዝግጅቱ በሦስቱ ወንጌላት ላይ ተመዝግቧል፡፡ (ማቴ.26፤17-19፣ ማር 14፤1-16፣ ሉቃ.22፤6-13) ፋሲካ ማለት ማለፍ ማለት ነው፤ ይኸውም እሥራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እሥራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይንም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፤ ሙሴም ለሕዝቡ ነገረ፤ ሁሉም እንደታዘዙት ፈጸሙ፤ መቅሰፍተ ከእግዚአብሔር ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የየግብጻውያን ቤት በሞተ በኵር ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት የእሥራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ ማለፉን ለማመልከት ነው፡፡ (ዘዳ.12፤1-13) በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እሥራኤላውያን በመጀመሪያ ወራቸው በዐሥራ ዐራተኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ ሀገራችንም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ይህ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡ በአንጻሩም ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ፋሲካ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት በዚህ በፋሲካ በዓል ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ደሙን ስላፈሰሰልን ነው፡፡ በደሙ መፍሰስ ሞተ በኵር የተባለ ሞተ ነፍስ ቀርቶልናልና፡፡ ‹‹ፋሲካችንም ክርስቶስ ነው፡፡›› (1ኛ ቆሮ.5፤6፣ 1ኛ.ጴጥ.1፤10)

                          ለ. በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ለደቀመዛሙርቱ
ረጅም ትምህርት አስተምሯል
ምሥጢረሥላሴየሦስትነት ትምህርት፤ምሥጢረሥጋዌ (የአምላክሰውመሆን)፤ በዮሐ.14፤16የሚገኘው በጠቅላላ የዚህ ዕለት ትምህርት ነው፡፡ የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎች ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንና የዳግም ምጽአቱ ነገርነው፡፡ እነዚህም በስፋትና በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳን፤በተአምራት ሊገልጥላቸው ሲችል በረጅም ትምህርትእንዲረዱት አድርጓል፡፡ ተማሪዎቹን እሱ እያስተማራቸው ሳለ ያገባቸውን እየጠየቁ ተረድተዋል፡፡ ከዚህም እያንዳንዳችን በቤተክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቆ መረዳት እንደሚገባን እንማራለን፡፡ 
ሐ.ይህ ዕለት ከደቀመዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባለ ጌታ ሆይ፣ መምህር ሆይ ብሎ በመሳም አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው  
       ጭፍሮቹም በዚሁ ዕለት ሌሊት የክብር ባለቤት የሆነውን ጌታችንን ይዘው ወደፊት፣ ወደኋላ እየጐተቱ፣ እያዳፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወስደውታል፡፡

ሰሙነ ሕማማት ዘረቡዕ

                     
                    ሰሙነ ሕማማት  ዘረቡዕ
                               ለምን የምክር ቀን  ተባለ?
                    የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑ፤ብዙውን ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ-መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ.26፤1-5፣ ቁ14-16፣ ማር.14፤1-2 ቁ.10-11፣ ሉቃ 22፤1-6)
           የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን ተሰብስበው ከእህል ከውኃ ተለይተው መላ ሰውነታቸውን የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ነገረ መስቀሉን የሚያወሳውን ሁሉ በመዘመርና በማንበብ እንዲሁም እስከ ሥርቀተ ኮከብ (እስከ ኮከብ መውጫ) በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከዚህ በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
                    መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን ቢዘህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ቤጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ዘመኗን ሰውነቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ ዕፍረት፣ ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ያለዋጋ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፤ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው፡፡
                                     የዕንባ ቀንም ይባላል
          ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ (ማቴ.26፤6-13፣ ማር.14፤3-9፣ ዮሐ.12፤1-8) ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

Tuesday, April 10, 2012

ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ

                     ሰሙነ ሕማማት  ማክሰኞ/የጥያቄ ቀን/
          ለምን የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል
   ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ-መቅደስ ምክንያት፣ በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ; ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ; የሚል ነበር፡፡ (ማቴ.21፤23-27፣ ማር.11፤27-30፤ ሉቃ.20፤1-8) እርሱም መልሶ እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች ከሰማይን; ወይስ ከሰው; አላቸው፤ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምሕርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸው ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡ ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባ ነው፡፡
            በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፤ የትምህርት ቀንም ይባላል፤ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፤ መክሮ መመለስእንደሚገባንሲገልጽልንነው፡፡(በማቴ.21፤23-27፣ማር.12፤2-13፤37፣ ሉቃ. 20፤9፣ 21፤38) የሚገኘው ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሙን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበት ይገባዋል፡፡

Monday, April 9, 2012

የሕማማት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሕማማት  ጥያቄዎችና  መልሶቻቸው
         1  በሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም አናማትብም ?               የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀለ ከተሰቀለ በኋላ ነው በሰሞነ ሕማማት  ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልገሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት  በሰሞነ ሕማማት በቤተክርስተያን  ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ የማማተብ  ስርዓት የለም
        2  በሰሞነ ሕማማት ለምን አንንሳሳምም?
           ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቶአል እኛም እንደ  ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችችንን ለማሰረዳት  ከዚሀ በተጨማሪም ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰሞነ ሕማማት እሰከ ምሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም
     3 በሰሞነ ሕማማት የማይፈቀዱ ሌሎቸ ነገሮች ምን ምን ናቸው ?        ማንኛውም ለስጋ የሚያደሉ ተግባሮችን መቀነስ እና ቢቻለን አበዛኛውን ጊዜአችንን በቤተ እግዚአብሔር የጌታን መከራ ሕማም  በማሰብ በፆም በስግደት በጸሎት ማሳለፍ 
                    በትዳር ያሉ በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ
                     ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ             
           4 ስለ ሰሞነ ሕማማት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ አለን?
  ነብዩ ኢሳይያስ
"በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሞአል " ኢሳ53፤4 ይላል ሕማማት የሚለው ቃለ በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወሰደ ሲሆን የጌታን መከራ የምናስብበት ሳምንት ነው የጌታችንን ሞቱን ሕማሙን ማሰብ መዘከር እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ እነዲህ ይላል    
       " ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና" 1ቆሮ11፤26 
               ይህ ሳምንት ለአይሁድና ለመሰሎቻቸው የደስታ ወቅት ቢሆንም ለክረስትያኖች በጥልቅ ኅዘን ውስጥ የሚገቡበት ሳምንት ነው እንዲሀ ተብሎ እንደተጻፈ'' እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ  ዓለም ግን ደስ ይለዋል እናንተም ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል''  ዮሐ16፤20 
                   በእርግጥ ኃዘናችን ትንሳኤውን እሰክናይ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም ግን እናዝናለን በትነሳኤው ደግሞ ደስታውን እንካፈላለን።
ሰኞ አይሁድ እንዴት እንደሚይዙት ለመማከር ክፉ ጉባኤያቸውን ጀመሩ
      ''በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች  የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ ጌታ ኢየሱስንም በተንኮል ሊያስይዙት ሊገሉትም ተማከሩ" ማቴ26፡3_4
 ይህንን ጉባዔ ቅዱሰ ዳዊት የከፉዎቸ ጉባዔ እያለ ይጠራዋል
     "ብዙ ውሾች ከበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ" መዝ21፤16
አይሁድ  ሰኞ የጀመሩትን  ዕረቡ ውሳኔአቸውን አጠናቀው በምሴተ ሐሙስ ከዕራትና ከቁርባን በኋላ ሰይፍና ጎመድ ይዘው መጡ በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ሰጣቸው ያዙትም እስከ አርብ ስድስት ሰአት ሲያንገላቱት ቆይተው ከበዙ መከራ በኋላ ሰቀሉት  ዘጠኝ ሰአት ላይ ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ከቅዱስ ስጋው ለየ ከአሰራ አንድ ሰአት በፊት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በምስጋና ገንዘው ቀበሩት ።
                              ከሕማሙ ከመከራው በረከት ያሳትፈን
                           ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

ሰሙነ ሕማማት ምን ማለት ነው ?

                                  ሰሙነ ሕማማት ምን ማለት ነው ? ክፍል1
        ቅድስት ቤተክርስቲያን ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙና ሕማማት (የሕማማት ሳምንት) በማለት ትዘክረዋለች፡፡ ሕማማት የሚለው ቃል ‹ሐመ፤ ታመመ› ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን፤
1/የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርት ነው፡፡
2/ በሌላም በኩል ይህ ሳምንት ከአዳምእስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነበሩ ነፍሳት በሲኦል የቆዩበት የአምስት ሺ አምስ መቶ የመከራ፤ የፍዳና የኵነኔ ዘመን መታሰቢያ ስለሆነ የሕማማት ሳምንት የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡
3/ እንደዚሁም ይህ ሳምንት ‹ቅዱስ ሳምንት›ይባላል፡፡ ከሌሎቹ ሳምንታት ሁሉየተለየየከበረነውና፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሳምንት በእያንዳንዱ ዕለት ስለ ፍጹምፍቅርየተከፈለየመሥዋዕትነት ሥራ ስለተሠራበት፤ የሰው ልጆች ድኅነት ስለተፈጸመበት፤ መድኃኔዓለም ስለእኛ ቤዛ ሆኖ ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆኖ ነፍሱን ስለካሰልን ‹ቅዱስ ሳምንት› ተብሏል፡፡
4/ በተጨማሪም ‹የመጨረሻ ሳምንት› ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በመዋዕለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነት፤ የአርአያነት ተግባራት ፍጻሜ በመሆኑ ነው፡፡
           በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምዕመናን በነግህ፤ በሠለስት፤ በቀተር፤ በተሰዓትና በሰርክ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጓዝ ስለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል የሚያዘክረውን ምዕራፍ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበብና በመጸለይ ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ ያሬድ በመጨረሻው ሳምንት በየዕለቱ በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈጸመውን ነገረ መስቀል በተመለከተ ያዘጋጀውን መዝሙር ይዘምራሉ፤ አብዝተው ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡
                           ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
          ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡
ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡ በእነዚህ የሕማማት ሳምንት ውስጥ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በየዕለቱ ያከናወናቸው የድኅነት ሥራዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
እሑድ፡- ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ‹ሆሺዕናህ› የሚል ሲሆን ትርጉሙም ‹እባክህ አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ ‹እባክህ አሁን አድን‹እባክህ አሁን አቅና፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡› (መዝ.117 25-26) የሆሣዕና በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ ተለይም አእሩግና ሕፃናት ‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም› በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሣዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተመሰገነው ምሥጋና ነው፡፡
             ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ ላይ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም ያድራል፤ የሕሊና ሰላምን ይሰጣል ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡
     ሰኞ፡አንጽሖተ ቤተመቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ ያድራል፡፡ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፤
በለስ የተባለች ቤተ-እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
          በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡
በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፤ ቤተመቅደስ፣ቤተጸሎት፣ ቤተመሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
           በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተ-ክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በሰድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
       ይቆየን